አዲሷ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር
ሰኞ፣ ሐምሌ 9 2004ማስታወቂያ
ህብረቱ ባለፈው ጥር ባካሄደው ጉባዔው ለኮሚሽኑ ሊቀመንበርነቱ ሥልጣን በተወዳዳሪነት በቀረቡት ካለፈው 2008 ዓም ወዲህ ኮሚሽኑንን በሊቀመንበርነት በመሩት ዣን ፒንግ እና በንኮሳዛና ድላማኒ ዙማ መካከል ለመምረጥ ያደረገው ጥረቱ ሁለቱም ዕጩዎች ሁለት ሦስተኛውን ድምፅ ባለማግኘታቸው ሳይሳካ ቀርቶ፡ ዣን ፒንግ ሥልጣኑን ያለፉትን ስድስት ወራት በተጠባባቂነት እንደያዙ እንዲቆይ ወስኖ እንደነበር አይዘነጋም። አዲሷ ሊቀመንበር በመላው አህጉር ሰላም የሚሰፍንበትን ሂደት የማበረታታት፡ በማሊ፡ በዴሞክራቲክ ሬፓብሊክ ኮንጎ የቀጠለውን የፖለቲካ ቀውስ የሚያበቃበትን መፍትሔ የማፈላለግ፡ እንዲሁም በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ዕርቀ ሰላም የሚወርድበትን ጥረት የማጠናከር ሥራ ይጠብቃቸዋል። ካለፈው ሰኞ ወዲህ በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ህብረት ጉባዔ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ