1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮ-ቴሌኮም ስኬታማ ነኝ ሲል፣ ደንበኞቹ አጥጋቢ አገልግሎት አይሰጥም ብለዋል

ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 2016

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 ስኬታማ የሰራ አፈፃፅም አድርጋለሁ ይላል DW ያነጋገራቸው ተገልጋዪች በተቃራኒው አገልግሎቱ ቢኖርም አጥጋቢ አይደለም ሲሉ ይናገራሉ።ኢትዮ-ቴሌኮም በአነስተኛ የሞባይል ቁጠባና ብድር አገልግሎት 5.3 ሚልየን ደንበኞች 12.88 ቢልየን ብድር ከ 2.1 ሚልየን ደንበኞች ደግሞ 13.35 ቢልዮን ብር መቆጠብ ችለዋል ተብሎል።

https://p.dw.com/p/4iAwg
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩምስል Hanna Demissie/DW

ኢትዮ-ቴሌኮም ስኬታማ ነኝ ሲል፣ ደንበኞቹ አጥጋቢ አገልግሎት አይሰጥም ብለዋል

ኢትዮ-ቴሌኮ በዚህ ሳምንት ባቀረበው የ2016 የበጀት ዓመት ዘገባ ብዙ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል። መስሪያ ቤቱ በዓመቱ ስኬታማ መሆኑን በዘገባቸው የገለጹት  ዋና ስራ አስፈፆሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት ብዙ ተግዳሮቶችም ገጥመውታል። ዋና ስራ አስ,ፈጻሚዋ ስኬቱን ቢያጎሉም ደንበኞች ግን አገልግሎቱ አጥጋቢ አይደለም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ሀና ደምሴ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ታቀርብልናለችየኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋዜጣዊ መግለጫ

« እንደ ተቁዋም መሪ ለኔ በተለይ የሚታየኝ  በዚህ "ዲጂታል አገልግሎት"  እያልን ባለንበት ዘመን ደንበኞቻቸን ማግኘት ባልቻሉት እና በተቋረጠባቸው አገልግሎት በኩባንያቸን ላይ የሚኖራቸው ቅሪታ ነው ሲሉ  የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናገሩ።ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይህንን የተናገሩት ኩባንያቸው የ 2016 አመት የስራ አፈፃፅም ለጋዜጠኞች በገለፁበት ወቅት ነው። 
በኢትዮ-ቴሌኮም የ2016 ዓ.ም. የበጀት አመት የስራ አፍፃፅም ሪፖርት   መሰረት   የተጣራ ትርፍ 21.79 ቢሊዮን  ብር ማግኘቱን አስታውቋል። ይህም  ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፅር  የ3.76 ቢሊየን ብር እድገት  አሳይቷል ብለዋል ዋና ስራአስኪያጅዋ ፍሬሕይወት ታምሩ  ።

የኢትዮ-ቴሌኮም መስሪያ ቤት
የኢትዮ-ቴሌኮም መስሪያ ቤት ምስል DW/H. Melesse


ኩባንያው የገንዘብ ዝውውርን በቴሌ ብር ዲጂታላይዝ በማድረግ በበጀት አመቱ 1.81 ትሪሊዮን የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ ዝውውር በቴሌ ብር የተከናወነ መሆኑንም አስረድተዋል ።
47.55 ሚሊዮን  የቴሌብር ተጠቃሚደ ንበኞች  አሉን ያሉት ስራ አስፈፃሚዋ ይህም በብሔራዊ ባንክ የመጋቢት 2016 ዓ.ም ሪፖርት መሰረት ቴሌብር በደንበኛ ብዛት ከአጠቃላይ የሀገሪቱ የሞባይል መኒ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የ45.7% ድርሻ መያዙ ተረጋግጧል ሲሉ ተናግረዋል ።የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ወደ ኢትዮጵያ እየመጣ ነው
 
የያዝነውአመት ባቀድነው መስረት በስኬት ብናጠናቅቅም ብዙ ተግዳሮቶች ነበሩብን ሲሉ የገለፁት ዋና ስራ አስፈፆሚዋ  የፅጥታ ችግር ፣ የውጭ ምንዛሪ ፣የኃይል  እና የእቃ አቅርቦት ችግሮች  ተደራርበው በፈለግነው መጠን መስራት  አላስቻለንም ሲሉ ገልፅዋል። በተለይ  ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች  በአማራ ክልል ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት  የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ካለቀ በኋላም እንኳን አለመጀመሩን  እና በዚህም ተቋሙ የደረሰበትን ኪሳራ እንዲያስረዱ ለቀረበላቸው  ጥያቂ ዋና ስራስኪያጀዋ ሲመልሱ «በነዚህ  አካባቢዎች የተፈጠረውየአገልግሎት መቋረጥ የፈጠረውን ኪሳራ መናገሩ እና ለደንበኞች ማሳወቁ ምንም ፋይዳ የለውም በሚል አድበስብሰውት አልፈዋል።የኢትዮ ቴሌኮም አዲስ የግንኙነት ማዕከል

ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 ስኬታማ የሰራ አፈፃፅም አድርጋለሁ ይላል  DW ያነጋገራቸው ተገልጋዪች በተቃራኒው አገልግሎቱ ቢኖርም አጥጋቢ አይደለም ሲሉ ይናገራሉ። ኢትዮቴሌኮም በአነስተኛ የሞባይል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት  5.3 ሚልየን ደንበኞች 12.88 ቢልየን ብድር   ከ 2.1 ሚልየን ደንበኞች ደግሞ  13.35 ቢልዮን ብር መቆጠብ ችለዋል ተብሎል።

ሀና ደምሴ

ኂሩት መለሰ

ፀሐይ ጫኔ