ኢትዮጵያ ወታደሮቿ ድንበር አቋርጠዋል የሚለውን የሶማሊያን ውንጀላ አስተባበለች
ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2016ሶማሊያ ስለ ኢትዮጵያ ወታደሮች ያቀረበችው ክስ ትክክል አይደለም መባሉ
በሶማሊያ ወቅታዊ ጉዳይ በመከረው የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የሶማሊያ ተወካይ የሆኑት ግለሰብ፣ የኢትዮጵያ ጦር ኢትዮጵያ ከሶማልያ ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች በሕገ-ወጥ መንገድ የሀገራቸውን ድንበር ጥሶ ከመግባት ባለፈ ከሀገሪቱ የፀጥታ ኃይላት ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጉንም ተናግረው ነበር።
ዘገባዎች እንዳመለከቱት ከሆነ ይህ ክስተት ቅዳሜ እለት የሆነ ሲሆን የኢትዮጵያ ወታደሮች ሒራን በተባለው የሶማሊያ ክልል ዘልቀው በመግባት አል ሸባብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ያሳያል።
አል ሸባብ ሰፊውን የሶማልያ ክፍል ተቆጣጥሮ በሚገኝባት ሶማሊያ ውስጥ በሀገሪቱ ሰላም በማስከበር ላይ ላለው የአፍሪቃ ሕብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (ATMIS) የጦር ሠራዊት ካዋጡ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ እስከ ሦስት ሺህ የሚደርሱ ወታደሮቿ የቡድኑን ጥቃት በመመከት ላይ ይገኛሉ።የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?
ይሁንና የኢትዮጵያ ወታደሮች የተባለውን ድንበር ጥሶ የመግባት ድርጊት አለመፈፀማቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣይ በሶማሊያ ሰላም ማስከበር ላይ የሚኖራት ሚና
በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ በቅርቡ ተልእኮውን የሚጠናቀቀው "የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ተልዕኮ በሶማሊያ" የተባለውን ጥምር ኃይልን ተክቶ በሚገባው ዓለም አቀፍ ሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ሠራዊት ስለሚኖረው ተሳትፎ ከሶማሊያ መንግሥት፣ ከአፍሪካ ሕብረትም ሆነ ከተባበሩት መንግሥታት የደረሰው ምንም ነገር እንደሌለ ቃል ዐቀባዩ አስታውቀዋል።
ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ በገባቸው ሶማሊያ በአፍሪካ ሕብረት የፀጥታ እና ሰላም ምክር ቤት ውሳኔ አግኝቶ፣ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ሲፀድቅ የሀገሪቱን ዋና ዋና መሠረተ ልማቶችን እና የመንግሥት ተቋማትን ለመጠበቅ ይሰማራል ተብሎ በሚጠበቀው አዲስ አለም አቀፍ ኃይል ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዳይካተቱ የሶማሊያ መንግሥት ከዚህ ቀደም ብሎ አቋሙን ይፋ አድርጓል።የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?
የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ የሶማሊያ የፀጥታ አማካሪ ናቸው በተባሉ ሰው ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የጀመረችውን የወደብ ጉዳይ የተመለከተ እንቅስቃሴዋን ካላቆመች አዲስ በሚሰማራው ሰላም አስከባሪ ኃይል ሀገራቸው የኢትዮጵያን ወታደሮች እንደማትቀበል መግለፃቸውን ኢትዮጵያ እና ራስ ገዝ ሶማሊላንድ ከተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነቱ ጋር ምንም የሚያያይዘው ነገር እንደሌለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢዩ ተድላ ከዚህ በፊትም ዛሬም ደግመው ተናግረዋል።የኢትዮ-ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩሳት ወዴት ?
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ማሳሰቢያ
ከዚሁ ከሶማሊያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተደረገውን የወደብ ተጠቃሚነት የሚያስገኝ የመግባቢያ ስምምነት ትታዋለች ወይም ሰርዛዋለች በሚል ትናንት በማሕበራዊ መገናኛ ዐውታሮች መሰራጨቱን ተከትሎ ሕዝብ እየተሰራጩ ካሉ ሀሰተኛ ይዘቶች እንዲጠነቀቅ ሲል መክሯል።
ጽሕፈት ቤቱ አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮችን በይፋዊ የመገናኛ ዘዴዎች ብቻ የሚያሰራጭ መሆኑንም አስታውቋል።
ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ሰለሞን ሙጨ
ነጋሽ መሀመድ
ፀሀይ ጫኔ