ኢትዮጵያ ዉስጥ የታገቱት ሰዎችና አጋቾች
ረቡዕ፣ ጥር 23 2004ማስታወቂያ
እራሱን የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ግንባር (አርዱፍ-በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ) የተሰኘዉ ቡድን ባወጣዉ መግለጫ ለእገታ-ግድያዉ ሐላፊነቱን ወስዷል።ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ታጋቾቹን በሐይል ለማስለቅ እንዳይኖክርም አስጠንቅቋል።ኢትዮጵያ የሚገኙት የአርዱፍ ባለሥልጣናት ግን በእገታዉም በመግለጫዉም የለንበትም ባዮች ናቸዉ።የገዳይ-አጋቾቹን ማንነት፥ታጋቾቹን የማስለቀቁን ጥረት-አንስቼ የምሥራቅ አፍሪቃና የመካከለኛዉ ምሥራቅ የፖለቲካ አዋቂ አቶ ዩሱፍ ያሲንን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።አጋቾቹ ማንናቸዉ? አርዱፍስ የትነዉ-የሚል ነበር።
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ