1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ዉስጥ ፆታዊ ጥቃት ለምን እየተባባሰ መጣ ?

ሐሙስ፣ መጋቢት 1 2014

«በሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት አይቶ፤ ሕግ ይከበርላቸዉ፤ መንግሥት ተገቢዉን ትኩረት ይስጣቸዉ ብዬ አንድ ሺ ጊዜ ስናገረዉ የነበሩትን ነገሮች መድገም አልፈልግም። የሚያዋጣዉ ራስዋን ያበቃች ሴት የሚፈጥሩ ተምረናል የሚሉ፤  ሰብዓዊነት ግድ ይለናል የሚሉ፤ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ፤ በጋራ ብቁ ሴትን የመፍጠር፤ አቅም ቢኖራቸዉ ጥሩ ነዉ።»

https://p.dw.com/p/48J11
Sudan, al-Qadarif Konflikt in Äthiopien - Flüchtlinge im Sudan
ምስል Marwan Ali/AP/dpa/picture alliance

ሴቶችን አፍኖ መዉሰድ፣ በደቦ መድፈር፣ ፊታቸው ላይ አሲድ መድፋት፣ ከየት የመጣ ጭካኔ ነዉ? እንደ ህብረተሰብስ ወዴት እየሄድን ነዉ?

  

« አሁን አሁን በሃገሪቱ ዉስጥ በሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት አይቶ፤ ሕግ ይከበርላቸዉ፤ መንግሥት ተገቢዉን ትኩረት ይስጣቸዉ፤ ፍትሃዊነት ይኑር ብዬ አንድ ሺ ጊዜ ስናገረዉ የነበሩትን ነገሮች መድገም አልፈልግም፤ አልችልምም። የሚያዋጣዉ ራስዋን ያበቃች ሴት የሚፈጥሩ፤ በሴቶች ጉዳይ ላይ አለን የሚሉ በሴቶች ጉዳይ ላይ እንሰራለን የሚሉ፤ ተምረናል የሚሉ፤  ሰብዓዊነት ግድ ይለናል የሚሉ፤ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ፤ በጋራ ብቁ ሴትን የመፍጠር፤ አቅም ቢኖራቸዉ፤ ሌሎች  ደግሞ ሌሎችን የመፍጠር አቅም  ይኖራቸዋል ማለት ነዉ።» ስትል የተናገረችዉ፤

Äthiopien I Konflikt in Tigray
ምስል Nariman El-Mofty/AP/picture allianc

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ን በማስመልከት፤ ለተጎዱ ዜጎች ድምፅዋን በማሰማትዋ የምትታወቀዉ መምህርት መዓዛ መሐመድ ከሰጠችን ቃለ ምልልስ የተወሰደ ነዉ። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ሰነበታችሁ። ከጎርጎረሳዉያኑ 1911 ዓ.ም ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቲት ወር መጨረሻ አካባቢ በጎርጎረሳዉያኑ የቀን ቀመር ማርች 8 የሚከበረዉ የዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ዘንድሮ ማለት ባለፈዉ ማክሰኞ ለ 111 ኛ ጊዜ ታስቦ ዉሎአል። በዓለም ሃገራት በሚታዩ ጦርነቶች ዉስጥ የመጀመርያዎቹ ተጠቂዎች ከእዉነት ቀጥሎ ሴቶች እና ሕጻናት እንደሆኑ ይነገራል። በሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነትም በተለይ ሴቶች ህጻናት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ብዙም ግፍ እንደተፈፀመባቸዉ የሃገር ዉስጥ የሰብዓዊ መብት ተከታካሪ ግለሰቦች፤ ድርጅቶች ብሎም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች አስታዉቀዋል።  በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶች ቀን ሲከበር፤ የሴቶች ወደ እኩልነት መምጣት፤ የመብት መከበር ንቅናቄዎች የሚታወሱበት ብሎም ወደፊትስ ምን መሥራት ይጠበቅብናል፤ የታዩትስ ለዉጦች ምን ያህል ናቸዉ የሚለዉን ጥያቄ ቆም ብለን የምናስብበት ቀን ነዉ ያለችን በኢትዮጵያ የሴቶች መብት ታጋይና የሴታዊት የጾታ እኩልነት ንቅናቄ መስራች ዶ/ር ስህን ተፈራ፤ በኢትዮጵያ ዉስጥ በሴቶች ላይ ጥቃት ስለመጨመር አለመጨመሩ በርግጥ የተጠና ጥናት የለም ስትል ገልፃለች።  

Frau im Zelt in Eritrea, wegen Landminen von Farm getrennt
ምስል AP Photo

ቤት ዉስጥ የሚታየዉን ጥቃት ኅብረተሰቡ ይታገሰዋል ብለዋል? ይህ ከባህል አንፃር የመጣ ነዉ ? ይህን ለመቅረፍ ትምህርት ወይም የግንዛቤ ማስጨበጫ ነገር ይካሄድ ይሆን? ዶ/ር ስህን ማብራርያ ሰጥታናለች። በሃገራችን የሴቶች ጥቃት በየጊዜዉ ብናዉራበትም፤ ቀላል ቢመስለንም፤ ሁሉ ሰዉ ኃላፊነቱን ቢወጣ ሊቀረፍ የሚችል ይመስላል እንጂ ፤  ኢትዮጵያ ዉስጥ እየሆነ ያለዉ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ አይነቱ ጨመረ ነዉ የመጣዉ ያለችን የዜጎች መብት ተቆርቋሪ መምህርት መዓዛ መሃመድ ናት።

ጾታዊ ጥቃት እየጨመረ የመጣዉ ማኅበረሰቡ ወንድን የሚያስቀድም በመሆኑ ፤ ከባህል አስታኮ የመጣ ይሆን? ተባብሶአል መባሉስ ለምንድን ይሆን? በኢትዮጵያ የሚታየዉን ብሎም ተባብሶአል የተባለዉን የፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ  የሴቶች መብት ታጋይ  ዶክተር ስህን ተፈራን እና መዓዛ መሐመድን አነጋግረናል። ሙሉ ጥንቅሩን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

 አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ