በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶች በፈረንሳይ የሚለማመዱበት ቅድመ ሥምምነት ተፈረመ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 8 2016ማስታወቂያ
በሚቀጥለው ዓመት በፓሪስ በሚካሔደው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ቅድመ ልምምዳቸውን በፈረንሳይ ሊያደርጉ የሚችሉበት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈረመ። ሥምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ከተማ ከንቲባ ዦን ኢቭ ሴኖ ናቸው።
ቅድመ ሥምምነቱ “ከታመነበት” በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አንቶኒ ወደ ተባለችው ከተማ ቀድመው በመጓዝ ልምምድ እንንደሚሰሩ ደራርቱ ቱሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያዊያን ስፖርት እና ባሕል ፌዴሬሽን በአውሮፖ ፌስቲቫል
አንቶኒ ከፓሪስ በስተደቡብ በ12 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኝ ነች። የፓሪስ ኦሎምፒክ ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2016 በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ሊካሔድ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል።
ሐይማኖት ጥሩነሕ
እሸቴ በቀለ