1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሮና በድሬደዋ

ዓርብ፣ መጋቢት 10 2013

በድሬደዋ አስተዳደር የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን የመስተዳድሩ ጤና ጽ/ቤት ዐስታወቀ። የሰው ሠራሽ መተፈንፈሻ መሣርያ ኦክስጅን እጥረት እንደገጠመውም አክሏል። የጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ለዶይቸ ቬለ (DW) በሰጡት መረጃ በመስተዳድሩ የኮቪድ 19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ዐስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/3qsgX
Deutschland Recklinghausen | Coronavirus | Sauerstoff für Beatmungsgeräte
ምስል picture-alliance/dpa/J. Güttler

በቂ የመተንፈሻ አጋዥ መሣርያ እና ኦክስጅን የለም

የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ለዶይቸ ቬለ (DW) በሰጡት መረጃ በመስተዳድሩ የኮቪድ 19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ዐስታውቀዋል።

በሆስፒታል ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ሰዎች ለማከም የሚያስችል በቂ አልጋ ቢኖርም የመተንፈሻ አጋዥ መሣርያ እና የኦክስጅን እጥረት መኖሩን ኃላፊዋ ተናግረዋል። ኅብረተሰቡ ስርጭቱን ለመከላከል የሚያስችሉ የጥንቃቄ መርኆዎችን መተግበር አለበት፤ ከዚያ በተጨማሪ ሕግ የሚያስከብረው አካልም ከምንግዜውም በላይ አሁን በአስገዳጅ ሁኔታ ሁሉንም ነገር ማስፈፀም እንዳለበት ወ/ሮ ለምለም አስገንዝበዋል። 

በድሬደዋ የኮቪድ ህክምና ማዕከል አስተባባሪ አቶ ትግስቱ የማነ በስርጭቱ ቁጥር መጨመር ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው ኅብረተሰቡ እና መስተዳድሩ ትኩረት መስጠት አለባቸው ብለዋል።

በቂ የመተንፈሻ መሣርያ እና ኦክስጅን አቅርቦት አለመኖሩ አስከፊ ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል እና መዘናጋት ከፍተኛ ዋጋ እንዳያስከፍል ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲደርግ ጠይቀዋል። በማዕከሉ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል መሆናቸውንም ተናግረዋል።

መሳይ ተክሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ