1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደሞዝ ያላገኙ የመንግሥት ሰራተኞች በሃዲያ ዞን

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2012

በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች «ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ ለወራቶች ባለማግኘታችን ለችግር ተዳርገናል» ሲሉ ቅሬታቸውን አሰሙ። የክልሉ ሕዝባዊ አገልግሎት እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ችግሩን እፈታለሁ ብሎአል።

https://p.dw.com/p/3UuAM
Wahl in Hosaena Äthiopien
ምስል DW/Y.-G. Egziabhare

ደሞዝ ያልተከፈለዉ ለማዳበሪያ ዕዳ ክፍያ በማዋሉ ነዉ ተብሎአል


በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች «ወርሃዊ የደሞዝ ክፍያ ለወራቶች ባለማግኘታችን ለችግር ተዳርገናል» ሲሉ ቅሬታቸውን አሰሙ ። ሰራተኞቹ ክፍያው ሊፈጸምላቸው ያልቻለው የሃዲያ ዞን ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ለሰራተኞች ደሞዝ የተያዘውን በጀት ለማዳበሪያ ዕዳ ክፍያ በማዋሉ ነው ይላሉ። የሰራተኞቹ ቅሬታ ትክክለኛ መሆኑን የጠቀሰው የክልሉ ሕዝባዊ አገልግሎት እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ችግሩን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመነጋገር እየፈታሁ ነው ሲል አስታውቋል።


ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ