1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወደ ውጪ ትሄዳላችሁ በሚል በኤጄንሲ የሚጭበረበሩ ሰዎች ጉዳይ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 10 2017

ወደ ውጪ አገራት ለስራ እንልካለን በሚል በህጋዊ መንገድ ፍቃድ አውጥተው በሚሰሩ ኤጄንሲዎች የተጭበረበሩ ሰዎች በደላቸዉን ይፋ እየተናገሩ ነዉ። ዶቼ ቬለ በተለያዩ ስፍራ የሚኖሩና ተጭበርብረናል ሰዎች እንዳነጋገረዉ፤ የኤጀንሲዎቹ ሰለባ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4oMcM
አዲስ አበባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ ምስል Solomon Muchie/DW

ወደ ውጪ ትላካላችሁ በሚል በኤጄንሲ የሚጭበረበሩ ሰዎች ጉዳይ

ወደ ውጪ ለስራ ትላካላችሁ በሚል በኤጄንሲ  የሚጭበረበሩ ሰዎች ጉዳይ

ወደ ውጪ አገራት ለስራ እንልካለን በሚል በህጋዊ መንገድ ፍቃድ አውጥተው በሚሰሩ ኤጄንሲዎች የተጭበረበሩ ሰዎች በደላቸዉን ይፋ እየተናገሩ ነዉ። ዶቼ ቬለ በተለያዩ ስፍራ የሚኖሩና ተጭበርብረናል ሰዎች እንዳነጋገረዉ፤ የኤጀንሲዎቹ ሰለባ ነን ሲሉ ተናግረዋል።   

ሰለባ ነን ያሉ አስተያየት ሰጭዎች እንdd,ተናገሩት፤ ኤጄንሲዎቹ ገንዘብ እያስከፈሉ ለተጎጂዎች ክትትል እንዳይመች በተለያዩ ጊዜያት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘዉን የመስሪያ ስፍራ አድራሻቸውን እየቀያየሩ ዱካቸውን የሚጠፉ ናቸው ብለዋል።

ወደ ሮማንያ ለስራ የመሄድ የመከነ ህልም

ፈይሴ ኦብሳ ትባላለች፡፡ ትውልድ እና እድገቷ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ሆሮጉዱሩ ወለጋ ጅማራሬ ወረዳ ነው፡፡ ፈይሴ በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ የኮሌጅ ትምህርቷን እየተከታተለች ሳለ በማህበራዊ ሚዲያ በአገሪቱ በሚታወቁ አርቲስቶች ጭምር የሚቀርብበት ማስታወቂያ ቀልቧል ይስባል፡፡ መልእክቱ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎች ሲተዋወቅ ቆይቶ በግሏም ሲደርሳት “በአውሮጳ፤ ሮማንያ አገር ያለ አጓጊ የስራ እድል ነው” የሚለዉ ማስታወቅያ፤ ፈይሴ እራሷንና በድህነት ውስጥ ያሉት ቤተሰቦቿን ለመቀየር በሚል ነገሩን ችላ ብላ ለማለፍ አልወደደችም፡፡ “ማንም ደሃ ልጅ ሰርቶ መቀየር እንደሚፈልግ ሁሉ እኔም ሰርቼ ለመቀየር ቤተሰቦቼንም ለመቀየር ፍላጎት ነበረኝ” የምትለው ተጎጂዋ ጉዳዩን ቀረብ ብላ ለመከታተል ስትሞክር እንደ ኤጀንሲዎቹወደ አውሮጳ ለመጓዝ 500 ሺህ ብር ብያስፈልግም በዱቤ አሁን 100 ሺህም ይሁን 50 ሺህ ብር በመክፈል ቀሪውን ከሄደች በኋላ እንደምትከፍል እንደተነገራት ተናግራለች፡፡ ድርጅቱ ንግድ ፍቃድ ያለው በመሆኑ እታለላለሁ ብላ እንዳልተጠራጠረች የምታስረዳው ፤ የአጭበርባሪ ኤጀንሲ ሰለባ የዛሬ ዓመት ግድም አራት ኪሎ ሄዳ መመዝገቧን ገልጻልናለች፡፡

የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቱ ከ12 ዓመታት በፊት ጀምሮ ስሙን እየቀያየረ እንደሚሰራም ይታወቃል የምትለው ተጎጂዋ፤ የዛሬ ዓመት ግድም 87 ሺህ ብር ከፍላ በስድስት ወር ውስጥ ስራ al, ወደተባለበት  ሮማንያ አገር የማትላክ ከሆነ ገንዘቧ ተመላሽ እንደሚሆን ተነግሯት ውል ከኤጀንሲዉ ጋር ብታስርም፤ ዛሬም ያም ሳይሆን በመቅረቱ “አሁን ላይ የትምህር ቤት ክፍያም ሆነ የታክሲ ክፍያ እንኳ አጥቼ ቤት ተቀምጫለሁ” ስትል በሃዘን አስረድታለች፡፡

በህክምና ሙያው አውሮፓ ሄዶ ለመቀጠር

ሌላው በህክምና ሙያ ላይ ተሰማርተው የሚያገለግሉት ቱራ አንሻ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ከሚኖሩበት ሻሸመኔ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ተመላልሰው፤ ኤጄንሲው ወደ አውሮጳ ልከንህ በሙያህ እንድትሰራህ እናደርጋለን በሚል ከተጠየቀው በኋላ 150 ሺህ ቅድሚያ ክፍያ 130 ሺህ በመክፈል ቢጠባበቁም ጠብ ያለ ነገር አላገኘሁም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “እኔ እንዳውም ስራም አለኝ፡፡ በርካታ የደሃ ልጆች አውሮጳ ለስራ ትሄዳላችሁ በሚል አይ.ኤም አልትራ ኢዱኬሽን የሚል ተቋም እኔ እንኳ ማውቃቸው ከ1000 በላይ ሰዎች በተለያየ ጊዜ የስራ ፈቃድና ቪዛ እየመጣ ነው በሚል ከፍተኛ ገንዝብ ስያስከፍል ቆይቷል፤ ሲሉ ግለሰቡ አክለዋል። ቦንቱ ታዬ የምትባል እኔ የማውቃት አንዲት የነቀምቴ ልጅ ቤተሰቦቿ ላይ ቤት ሽጣ 700 ሺህ ብር ከፍላ ሜዳ ላይ በመቅረቷ በመጨረሻ እራሷን አጥፍታለች፡፡ ሥነ-ልቦናቸው ተጎድቶ መንገድ ላይ ቀሩ ብዙ ናቸው” ብለዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ ምስል Solomon Muchie/DW

ከስድስት ዓመታት በፊት የተጀመረው..

በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ በአንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ የምትሰራ ትዕግስት ጉልላት የተባለች ግለሰብም በተለያዩ ጊዜያት ስሙን ይቀያይራል ባሉት በዚሁ ኤጄንሲ ወደ ፖላንድ ከዚያም ወደ ጀርመን እና ሮማንያ ለመላክ ከ6 ዓመታት በፊት 150 ሺህ ብር ብትከፍልም እስካሁንም ከብሯም ሆነ ከተመኙችው የስራ እድል ሳትሆኑ መቅረትዋን ተናግራለች። “በተመሳሳይ መልኩ የተታለሉ ልጆች 1000 አባላት ያለው ቴሌግራም ቡድን ከፍተን ነበር” ያለችው ትዕግስት ጉዳዩን አሳፋሪ ስትል አስተያቷን አክላለች፡፡

ዶይቼ ቬለ ተበደልን ባሉት ከተለያዩ አከባቢዎች አስተየታቸውን በሰጡን መሰረት የኤጄንሲው ባለቤት ናቸው የተባሉትን ግለሰብ በስልካቸው ደውለን ማግኘት አልቻለም፡፡ እንደ አስተያየት ሰጪ ተበዳዮች ስሙንና አድራሻውን እየቀያየረ ይንቀሳቀሳል ያሉት ድርጅት አሁን አድራሻው የት እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ተጭበርብሬናል ያሉት ግለሰቦቹ በተለያዩ ጊዜያት ለፖሊስ ቢያመለክቱም እልባት እንዳላገኙ አስረድተዋል፡፡ ቅሬታ ስለቀረበበት ጉዳይ ፖሊስ የሚያውቀው ነገር ካለ በሚል ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ጥያቄውን አቅርበን መረጃ እንደሌላቸው በመግለጽ ተጎጂዎች መረጃውን ይዘው ቀርበው ለፖሊስ ኮሚሽን እንዲያመለክቱ መክረዋል፡፡    

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ