ዜሌንስኪ ኼርሶንን ጎበኙ
ሰኞ፣ ኅዳር 5 2015ማስታወቂያ
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ ከጥቂት ቀናት በፊት ከሩስያ ኃይሎች ነፃ የወጣችውን የኼርሶን ከተማን ጎብኙ። ስምንት ወራት
ፕሬዚዳንቱ ለስምንት ወራት በሩሲያ ኃይሎች ወረራ ስር የነበረችዉ ከርሰን ነዋሪዎች ያለ ኤሌክትሪክና የቧንቧ ውኃ አገልግሎት እንዴት እንደሚኖሩ አስከፊዉን ሁኔታ በዓይናቸዉ አይተዋቷል።
ዜለንስኪ በአካባቢው ላይ የጦርነት ወንጀሎች እንደተፈጸሙ የሚጠቁሙ ምልክቶች እንዳሉም ተናግረዋል። ዜሌኒስኪ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤
«መርማሪዎች የሩሲያ የጦር ከ400 በላይ ወንጀሎችን መፈፀማቸዉን መዝግበዋል። የሰላማዊ ነዋሪዎችም ሆነ የጦር ሠራዊት አስከሬን እየተገኘ ነው ። የሩስያ ጦር ሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ወሮ አረመኔነት እንደፈፀመዉ ሁሉ በኼርሶንም አረመኔነት መፈፀሙ ታይቷል።»
ዜሌንስኪየ የከርሰን ነጻ መውጣት "የጦርነቱ ማብቃት መጀመሪያ" የሚል ምልክት እንደሆነም ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የኔቶ ዋና አዛዥ ጄንስ ስቶልተንበርግ ለዩክሬናዉያን ገና አንዳንድ ፈታኝ ወራቶች እንደሚጠብቃቸው ሳይገልፁ አላለፉም ። የሩሲያ ወታደሮች ተሸንፈዋል ተብሎ ችላ ሊባል እንደማይገባም አክለዋል።