Tesfalem Waldyes Eragoሰኞ፣ ግንቦት 6 2010በዕለቱ የዜና መጽሔት በኢትዮጵያ መንግስት እና ኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር መካከል እየተካሄደ ነው ስለተባለው ንግግር የተጠናቀረ ዘገባ ቀዳሚ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ስላሉ ተቃውሞዎች የሚመለከተው ዘገባ በተከታይነት ይቀርባል፡፡ በኢትዮጵያ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስታወቁን የተመለከተ ጥንቅር ይከተላል፡፡ አሜሪካ የእስራኤል ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሯን በተመለከተ በስፍራው ከሚገኝ ወኪላችን ጋር የተደረገ ቃለምልልስም ተካትቷል፡፡