1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች

ሐሙስ፣ ሐምሌ 6 2015

በሀዋሳ ከተማ የሞዴሊንግ ሙያ ሥልጠና እየወሰዱ ከሚገኙት መካከል ታዳጊ ትህትና ዱካሞ (11) እና ረድኤት አበራ (15) ይጠቀሳሉ፡፡ ትህትና እና ረድኤት በሞዴሌግ ለመሠልጠን የተነሳሱት በሙያው ከፍ ያለ ቦታ የደረሱ ወጣቶችን በምሳሌነት በማየት እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡

https://p.dw.com/p/4ToZj

የሞዴሊንግ ሥልጠና በሚያደርጉበት ወቅት ቤተሰቦቻቸውና የቅርብ ጓደኞቻቸው በጎ አስተያየት እንደሚሰጧቸው የሚናገሩት ትህትና እና ረድኤት “ ሥለ ሞዴሊንግ የተሳሳተ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎችም ያጋጥሙናል “ ይላሉ፡፡  በሳምንት ሶስት ቀን ነው የምንሰለጥነው የምትለው ረድኤት ስልጠናው የራስ መተማመኗን እንድታጎለብት እንደረዳት ትናገራለች። ትህትና ከስልጠና አልፋ በዘርፉ መስራትም ጀምራለች። ሁለቱም በዚህ ሙያ ዝነኛ መሆን እና ኢትዮጵያን ወክለው መወዳደር ይሻሉ። #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute


ዘጋቢ ፡ ሊሻን ዳኜ
ቪዲዮ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ