1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የህክምና ባለሙያዋ ተሞክሮ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2012

በመላው ዓለም በኮቪድ 19 ከ4,2 ሚሊየን ሰዎች በላይ መዛቸው ዛሬ ይፋ ሆኗል። ሕይወታቸውን ያጡት 286 ሺህ ሰዎች ደርሰዋል፤ ከ1,5 ሚሊየን የሚበልጡት ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል። ካለፈው ታኅሣስ ወር አጋማሽ አንስቶ ቀስ በቀስ የዓለም ስጋት በሆነው የኮሮና ተሐዋሲ የሚያዙት ቢበረክቱም ታምመው የሚድኑትም ወገኖችም ቁጥር ቀላል አይደለም።

https://p.dw.com/p/3c8Ii
Symbolbild Corona-Virus Impfstoff
ምስል picture-alliance/dpa/Geisler-Fotopress

«የኮቪድ 19 ምልክቶች ከሰው ሰው ይለያያሉ»

በዓለማችን የተለመደውን የሰዎች የዕለት ተዕለት መስተጋብር ሳይታሰብ ድንገት የለወጠው ወረርሽኝ ከተከሰተ ወራት ተቆጠሩ። በየሀገሩ በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር የመጨመሩ ዜና የብዙዎችን ቀልብ በመያዙ ከበሽታው ይበልጥ ሰዎች ስጋቱ እንደከበደባቸው የሚያመለክቱ ማሳያዎች ጥቂት አይደሉም። ለወትሮው እንደየባህሉ ሲያነጥሱ ጤናና ረዥም ዕድሜ ይመኝ የነበረው ወገን በዘመነ ኮሮና ምንመሆኑ ነው በሚል ሲገረምምዎ ሲመለከቱ በእርግጥም ጊዜው መለወጡን ልብ ይሏል። 

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጀርመን ውስጥ ተጠናክሮ የተከሰተው ባለፈው መጋቢት ወር ነበር። በወቅቱ የዜጎች እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ቢጣልም የህክምና ተቋማት ሥራ አስቸኳይ ላልሆኑ የጤና ችግሮች ቀጠሮ ቢሰጥም ለድንገተኛ ህመምም ሆነ በኮሮና ተሐዋሲ ለተያዙ ታማሚዎች የሚሰጠዉ ርዳታ ቀጥሏል። እዚህ ጀርመን ሀገር የህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉና የውስጥ ደዌ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሰብለወንጌል ይመኔ፤ ከኮሎኝ ከተማ በመኪና 20 ደቂቃ ተጉዘው በምትገኘው ኤንግልስ ኬርሸ በተሰኘች አነስተኛ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በመሥራት ላይ ናቸው። ተሐዋሲው ጀርመን ውስጥ በተስፋፋ ሰሞንም ወደዚህ ሀኪም ቤት ታማሚዎች በመምጣታቸው እሳቸውና ባልደረቦቻቸው የሙያ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ ሳሉ ለተሐዋሲው ተጋለጡ። ከበሽታው ማገገም የሚያስችላቸውን ተገቢውን ሁሉ አድርገው አሁን ጤናቸው የተመለሰው የህክምና ባለሙያ ተሞክሯቸውን አጋርተውናል። ለመሆኑ የመተላለፊያ መንገዱም ሆነ የሚያሳየው የህመም ምልክት ገና ተጠንቶ ያላለቀው ኮቪድ 19 ከህመሙ ያገገሙት እንዴት ይገልፁታል? እጅን በሳሙና ደጋግሞ መታጠብ፤ አፍና አፍንጫን መሸፈን፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅን አንዘንጋ። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው አድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ