Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ኅዳር 21 2017ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከመንግሥታቸው የሚዋጉ ታጣቂዎች “አንድ ሺሕ ዓመት ቢታገሉ ስለማያሸንፉን፤ ያኛውን መንገድ ጥለው ወደ ሰላም እንዲመጡ” የሚል ጥሪ አቀረቡ። የኬንያ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከዩጋንዳው አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ከሶማሊያ ለማሸማገል እገዛ እንደሚያደርጉ አስታወቁ። በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ታጣቂዎች ዘጠኝ ሰዎች መግደላቸውን ተከትሎ “መንግሥት ለደህንነታችን ሊደርስ ይገባል” ሲሉ ነዋሪዎች ጥሪ አቀረቡ። ፈረንሳይ ለምርምር በሚል ከ40 ዓመታት በላይ ይዛ ያቆየቻቸውን ወደ 3,500 የሚጠጉ የአርኪዮሎጂ ቅርሶች ለኢትዮጵያ አስረከበች።