የመሬት መንሸራተት በሲዳማ ክልል
ሰኞ፣ መስከረም 18 2013ማስታወቂያ
በሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ በደረሰ የመሬት መናድ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው ባለስልጣናት አስታወቁ። ባለሥልጣናቱ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ( DW ) እንዳስታወቁት አደጋው ትናንት ቀትር ላይ የደረሰው በወረዳው ሚጢቾ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ ነው። በአሁኑ ወቅት እየጣለ ከሚገኘው ዝናብ ጋር ተከትሎ በቀጣይ ተመሳሳይ ጉዳቶች ሊከሰቱ ይችላል የሚል ስጋት ማሳደሩን የሚናገሩ የወረዳው ባለሥልጣናት በተለይ በከፍታማ አካባቢ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲሉም አሳስበዋል ። ከሐዋሳ ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ