1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመሬት ናዳው በመቶዎች የሚቆጠሩትን ከቄዬአቸው አፈናቅሏል

ቅዳሜ፣ ግንቦት 1 2012

በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ ጎሮዜ በተባለ ቀበሌ ትናንት የደረሰውን የመሬት ናዳ ተከትሎ ነዋሪዎች አካባቢውን በመልቀቅ ላይ ይገኛሉ።የልዩ ወረዳው መስተዳድር አንዳስታወቀው በቀበሌ የተሰነጠቁ በመታየቱ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን አካባቢውን አንዲለቁ እየተደረገ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/3bymI
Erdrutsch Äthiopien Oromia Region West Arsi Zone
ምስል West Arsi Zone Government Communication Affairs Office

በደቡብ ክልል የተፈጠረው የመሬት መንሸራተት በርካቶችን ከቄዬአቸው አፈናቅሏቸዋል።

በደቡብ ክልል አሌ ልዩ ወረዳ ጎሮዜ በተባለ ቀበሌ ትናንት የደረሰውን የመሬት ናዳ ተከትሎ ነዋሪዎች አካባቢውን በመልቀቅ ላይ ይገኛሉ።የልዩ ወረዳው መስተዳድር አንዳስታወቀው በቀበሌ የተሰነጠቁ በመታየቱ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችን አካባቢውን አንዲለቁ እየተደረገ ይገኛል።በትናንቱ ናዳ አሁንም ከመሬት በታች ተቀብረው የሚገኙ ቀሪ አምስት ሰዎችን የመፋላለጉ ጥረት ዛሬ ለሁለተኛ ቀናት ሲከናወን ቢውልም አስከአሁንተጎጂዎቹን ማግኘት አንዳልተቻለ የልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካራ ማሞ ለዶቼ ቨለ ( DW ) በስልክ ገልጸዋል።

Erdrutsch Äthiopien Oromia Region West Arsi Zone
ምስል West Arsi Zone Government Communication Affairs Office

 ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ታምራት ዲንሣ