Eshete Bekeleቅዳሜ፣ መስከረም 18 2017ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የተፈራረመችው የመግባቢያ ሥምምነት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ይጥሳል ሲሉ ከሰሱ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሀገራቸው “ዓላማ በቀጠናው የጋራ ዕድገት እና ብልጽግና መፍጠር” እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች በተራዘመ የብድር አቅርቦት የመጀመሪያ ግምገማ ተስማሙ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በምትገኘው አል-ፋሽር ለሁለት ቀናት በፈጸመው ጥቃት 48 ሰዎች ተገደሉ። የሊባኖሱ ሒዝቦላሕ መሪው ሐሳን ናስረላሕ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጠ።