1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«መንግሥት የወሰደው አቋም ተቋማቱ ነፃ ሆነው እንዳይሰሩ ማስፈራሪያ መሆኑን ያሳያል»

ሰኞ፣ ጥቅምት 26 2016

የኮሚሽኑ መግለጫ "አስተማማኝ መረጃ ላይ ያልተመሰረትና ሚዛናዊነት የሚጎድለው ነው" ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ውድቅ አድርገውታል። "መንግስት የተቋሙን ገለልተንነት አበክሮ ይሻል፡፡ ገለልተኝነቱ ግን ከመንግስት ብቻ ሳይሆን ከባዕዳንም ጭምር ነው" ብለው ነበር።አንድ የመብት ተሟጋች ይህ አቋም መታረም አለበት ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4YSyG
በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ለሌሎች መገናኛ ብዙኃን የሰጡ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መሪዎች መንግሥት ኢሰመኮ ያወጣውን መግለጫ ወደማረም ከመሄድ ይልው ውድቅ ማድረጉ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው ውጤቱ አወንታዊ ድጋፍ እንደማይኖረው ገልፀዋል።
ከዚህ በፊት ጦርነት በነበረበት ወቅት የሰላም ጥሪ ያቀርቡ የነበሩ የሲቪክ ድርጅቶች ለሰላም ጥሪ በማድረጋቸው ምክንያት በመንግሥት ባለስልጣናት ይሰደቡ ነበር ያሉት አቶ በፍቃዱ ኃይሉ በተለይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ቢሮዎችን በመዝረፍ የተደረገው ወንጀል እና ለምርመራ ሥራ የወጡ የዚሁ የኢሰመጎ ሰራተኞቹ ተይዘው የታሰሩበትን ክስረት በአብነት በመጥቀስ የመብት መከበር እና የዴሞክራሲ ባህል ማደግ ላይ የሚሰሩትን ማስፈራራት የተልመደ ነው ብለዋል።ምስል Solomon Muche/DW

የመንግሥት ኮምኒኬሽን ባለሥልጣን ለኢሰመኮን ማሳሰቢያ መስጠቱ ተገቢነት አይደለም ሲሉ የመብት ተሟጋቾች ወቀሱ


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል ድሮንን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን እና 200 ሴቶች መደፈራቸውን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ውድቅ ማድረጉ ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉ በመብቶች ጥበቃ ላይ የሚሠረ ተቋማት ገለፁ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተጠሪነታቸው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆኑ ተቋማት ላይ መሰል አቋም መያዙ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ማህበረሰብ እፈጥራለሁ ከምትለው ሕልሟ ጋር የሚጋጭ መሆኑን የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ሥራ አስፈፃሚ በፍቃዱ ኃይሉ ገልፀዋል።በአማራ ክልል ንፁሐን በድሮን ድብደባ ተገድለዋል - ኢሰመኮ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ የኮሚሽኑን ለግል ጫ "አስተማማኝ መረጃ ላይ ያልተመሰረትና ሚዛናዊት የሚጎድለው" በማለት ኮሚሽኑ ተገቢውን እርምት እንዲወስድም አሳስበው ነበር።ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው መንግሥት የወሰደው አቋም "ተቋማቱ ነፃ ሆነው እንዳይሰሩ ማስፈራሪያ እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ መሆኑን ያሳያል" ብለዋል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ መንግሥት ስለሰጠው መግለጫ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
በአማራ ክልል ለወራት በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት ድሮንን ጨምሮ በከባድ የጦር መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ሕይወት የቀጠፉ ጥቃቶች በንፁሃን ሰዎች ላይ ሞትን ጨምሮ የአካል ጉዳት መድረሱን በማስረጃ አስደግፎ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ በመንግሥት ውድቅ ተደርጓል።  ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የት አካባቢ ፣ መቼ ፣ ምን ያህል ሰው የድሮን ጥቃት ሰለባ እንደሆነ በዝርዝር አስቀምጧል ፣ ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የጤና ባለሙያዎችን እና ተፈናቃዮችን ጨምሮ ቢያንስ 200 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሰለባ እንደሆኑ ዘገባው ጠቅሷል።ይህ የኮሚሽኑ መግለጫ "አስተማማኝ መረጃ ላይ ያልተመሰረትና ሚዛናዊነት የሚጎድለው ነው" ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ውድቅ አድርገውታል።ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ብቻ እንዲወሰን ለመንግስት ጥሪ አቀረበ "መንግስት የተቋሙን ገለልተኝነት አበክሮ ይሻል፡፡ ገለልተኝነቱ ግን ከመንግስት ብቻ ሳይሆን ከባዕዳንም ጭምር ነው" ሲሉ ተናግረው ነበር።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማዕከል ሥራ አስፈፃሚ በፍቃዱ ኃይሉ "በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ እንዲህ ያለው ነገር የተለመደ" መሆኑን እና መታረም ያለበት እንደሆነ ገልፀዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ የሲቪክ ድርጅቶች ፣ የሕግ ተቋማት፣ በሴቶች ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች አስተያየት ለመስጠት ሲሸሹ አስተውለናል። ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ለ ዴሞክራሲ የተባለ ሲቪክ ድርጅት ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ ታደለ ደርሰህ በመንግሥት የተያዘው አቋም " ተቋማቱ በተቻለ መጠን ገለልተኛ እንዳይሆኑ የሚደረግ ጥረት መሆኑን ያሳያል" ብለዋል።ከእናቶቻቸው ጋር የሚታሰሩ ሕጻናት አያያዝ “አሳሳቢ” እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀከዚህ በፊት ጦርነት በነበረበት ወቅት የሰላም ጥሪ ያቀርቡ የነበሩ የሲቪክ ድርጅቶች ለሰላም ጥሪ በማድረጋቸው ምክንያት በመንግሥት ባለስልጣናት ይሰደቡ ነበር ያሉት አቶ በፍቃዱ ኃይሉ በተለይ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ቢሮዎችን በመዝረፍ የተደረገው ወንጀል እና ለምርመራ ሥራ የወጡ የዚሁ የኢሰመጎ ሰራተኞቹ ተይዘው የታሰሩበትን ክስረት በአብነት በመጥቀስ የመብት መከበር እና የዴሞክራሲ ባህል ማደግ ላይ የሚሰሩትን ማስፈራራት የተልመደ ነው ብለዋል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ለሌሎች መገናኛ ብዙኃን የሰጡ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መሪዎች መንግሥት ኢሰመኮ ያወጣውን መግለጫ ወደማረም ከመሄድ ይልው ውድቅ ማድረጉ አሳሳቢ መሆኑን ጠቅሰው ውጤቱ አወንታዊ ድጋፍ እንደማይኖረው ገልፀዋል።

 "መንግስት የተቋሙን ገለልኝነት አበክሮ ይሻል፡፡ ገለልተኝነቱ ግን ከመንግስት ብቻ ሳይሆን ከባዕዳንም ጭምር ነው" ሲሉ ተናግረው ነበር።
ይህ የኮሚሽኑ መግለጫ "አስተማማኝ መረጃ ላይ ያልተመሰረትና ሚዛናዊነት የሚጎድለው ነው" ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሠ ቱሉ ውድቅ አድርገውታል። ምስል Seyoum Getu/DW
ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ በክልሉ የት አካባቢ ፣ መቼ ፣ ምን ያህል ሰው የድሮን ጥቃት ሰለባ እንደሆነ በዝርዝር አስቀምጧል ፣ ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ የጤና ባለሙያዎችን እና ተፈናቃዮችን ጨምሮ ቢያንስ 200 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሰለባ እንደሆኑ ዘገባው ጠቅሷል።
በአማራ ክልል ለወራት በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት ድሮንን ጨምሮ በከባድ የጦር መሣሪያዎች በተሰነዘሩ ሕይወት የቀጠፉ ጥቃቶች በንፁሃን ሰዎች ላይ ሞትን ጨምሮ የአካል ጉዳት መድረሱን በማስረጃ አስደግፎ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ በመንግሥት ውድቅ ተደርጓል።  ምስል Solomon Muche/DW

 

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ