ማስታወቂያ
ኬንያ የዕለት ማረፊያ የተቸገሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መጠለያ አልባ ሰዎች ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ ጥሩ ገንዘብ የሚያስገኝ ሞያ ያላቸው ሰዎች ይገኙበታል። አንዳንዶች በአነስተኛ ገንዘብ ምሽታቸውን ለማሳለፍ ሲፍጨረጨሩ አንዳንዶቹ ደግሞ ከጎዳና በማይሻል ሁኔታ በየስርቻው ሰብሰብ ብለው ያድራሉ ። በዚህ ሁኔታ የሚመጡ ሰዎችን ተቀብለው የሚስተናግዱም እንዲሁ አልጠፉም። በዚህ የቪዲዮ ዘገባ የመኪና ጋኙ መካኒክ እና የልብስ ነጋዴው የአንድ ምሽት አዳራቸውን ማግኘት ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ይነግሩናል ።