Eshete Bekeleእሑድ፣ ሰኔ 16 2016በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ለ6ኛው ሀገር አቀፍ የቀሪ እና የድጋሚ ምርጫ ነዋሪዎች ድምጽ ሲሰጡ ዋሉ። ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መንግሥታቸው ተግባራዊ በሚያደርገው የግብር ጭማሪ ላይ በኬንያ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ካካሔዱ ወጣቶች ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን አስታወቁ። የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ከመስከረም 26 ቀን 2016 ጀምሮ በጋዛ ሲካሔድ በቆየው ውጊያ ላይ “ወሳኝ” ለተባለ ንግግር ወደ አሜሪካ አቀኑ። የኬንያ ኃይሎች ማክሰኞ በወሮበሎች ወደምትታመሰው ሔቲ እንደሚዘምቱ የሀገሪቱ መንግሥት እና የፖሊስ የመረጃ ምንጮች ተናገሩ። በሩሲያ እና ዩክሬን ጥቃቶች ሰዎች ተገደሉ