የሱዳን ጎረቤቶች ጉባኤ
ዓርብ፣ ሐምሌ 7 2015ካርቱምን የጦር አውድማ በማድረግ የሱዳንን ሀገረ መንግስት በፍጥነት እያፈራረሰና በአካባቢው አገሮች ላይም ቀውስ እየፈጠረ ባለው የሱዳን ጦርነት ላይ ለመመከር፤ ካይሮ ላይ በግብጹ መሪ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ የተጠሩት የሱዳን ጎረቤት አገሮች መሪዎች፤ ትናንት ክስብሰባው በኋላ በጋራ ባወጡት መግለጫ ፤ የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች ባስቸኳይ ተኩስ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፤ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ የውጭ ሀይሎችና መንግስታት በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመገባት እንዲቆጠቡም ጥሪ አቅርበዋል። የሰባዊ እርዳታ የሚደርስበትን ሁኒታ ሁሉም ወገኖች እንዲያመቻቹና ዋስትናም እንዴዲሰጡ በመጠየቅም የጎረቤት አገሮቹም የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። በስብሰባው የሊቢያ፤ ቻድ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ፤ ደቡቡ ሱዳን፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ መሪዎች የተገኙ ሲሆን፤ሁሉም የሱዳን ጎረቤት አገሮች ባንድ ላይ ተሰብሰበው በሱዳን ላይ ሲመክሩ ይህ ግብጽ የጠራቸው ስብሰባ፤ የመጀመሪያውና ከፍተኛ ግምት የተሰጠው እንደሆነም ተገልጿል።
ቀደምሲል የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች በአሜሪካና ሳኡዲ አረቢያ ሸምጋይነት በተደጋጋሚ ግዚያት የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ ደርሰው የነበር ቢሆንም አንዱም ግን ተከብሮ እንደማያውቅ ነው የሚታወቀው። ካሳምንት በፊትም በዚሁ በሱዳን ቀውስ ላይ ለመምከር በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስትት ኢጋድ በተጠራው ስብሰባም ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖቾ ተጋብዘው የነበር ቢሆንም፤ ሁለቱም ግን በስብሰባው አልተገኙም። በአሁኑ የክይሮ ስብሰባ ደግሞ፤ ሁለቱም ወገኖች እንዳልተጋብዙ ነው የተገለጸው። ዋናዎቹ ተፋላሚ ወገኖቾ ች ያልተገኙበት ወይም ያልተጋበዙበት የሰላም ስብሰባ ውጤታማ መሆኑን የሚጠራጠሩ የፖለቲክ ተንትኖችና ሱዳናውያን አክቲቪስቶች፤ ለካይሮው ስብሰባ በጎ እሳቤዎችና የሰላም ጥሪዎች ተግባራዊ ምላሽ መገኘቱን ይጠራጠራሉ። በጦርነቱ ተፈናቅላና ተስዳ በአሁኑ ወቅት በለንደን የምተገኘው ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ዳሊያ አብደልመነን እንደምትለውም፤ ዋናዎቹ የጦርነቱ አዝማቾችና ሱዳናውያን ባለድርሻ አካላት ያልተሳተፉበት የሰላም ስብሰባ፤ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱ አጠራጣሪ ነው። “ብዙ ስብሰባዎችን መጥራትና ማስተናገድ ይቻላል። ግን የሚፋለሙ ወገኖቾ ጦርንቱን ለማስቆም ፋላጎት ከሌላቸው የተወሰኑ የጎረቤትም ይሁን ሌሎች አገሮች መሪዎች ለስብሰባ መቀመጣቸው በሱዳን ያለውን ሁኔታ አይለውጠውም” በማለት ትከራከራለች።
ጅዮርጂዮ ካፌሮ የተባሉ በገልፍ ባህረ ሰልጤ አገሮች ላይ የፖቲካ ተንታኝም፤ የጋዜጠኛ ዳሊያን ስጋት ይጋራሉ። ግብጽ ይህንን ጉባኤ የጠራችበት ምክኒያት በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ላይ ጫና ለመፍጠር አካባቢያዊና አለማቀፍዊ ትብብር የሚያስፈልግ መሆኑን በማኗ ሊሆን ይችላል በማለት፤ ከተፋላሚ ወገኖች በተጨማሪ ሌሎች ወገኖችም ቢካፈሉ ጥሩ የነበር መሆኑን ያምናሉ።፡ “የሁለቱ ተዋጊ ወገኖች በስብሰባው አለመገኘት የራሱ ችግር አለው። የሲቪልና በተለያዩ ማህበረሰቦች ቅቡልነት ያላቸው የልዩ ልዩ ማህበረሰቦች ተወካዮችም አለምመኘታቸው ሌላው ጉድለት ነው በማለት ከዚህ አልፎ የገልፍ ባህረሰላጤ አሮች ተሳትፎም አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል
የሱዳን ችግር መዘዘዙ ለብዛዎቹ የአፍሪካና የገልፍ ባህረሰላጤ አገሮች ጭምር የሚተርፍ እንደሚሆን ይታመናል። በማንነት ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች ስይቀር የተፈጸሙባት መሆኑን የሚያረጋግጡ የጅምላ መቅብሮች ተግኝተውባታል የምትብለው ሱዳን፤ በዚህ ጦርነት ተገፍታ መንግስት አልባ ክሆነች ከሊቢያ በባሰ የጦር አበጋዞች መነሃሪያ፤ የአክራሪዎች መደበቂያና መተላለፊያ ልትሆን እንደምትችል ብዙዎች ያምናሉ።
ይህ ስጋት በተለይ ለግብጽ የተለየ ሊሆን ቢችልም ሁሉም የጉባኤው ተሳታፊ መሪዎች ይህንን አደጋ የተገንዘቡት መሆኑን ባደረጓቸው ነግግሮች አንጸባርቀዋል።። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል ተጨማሪ እርምጃዎችንና ተነሳሽነቶችን እንዲስወስዱ መወሰናቸውም ጉዳዩን የያዙበትን ደርጃ የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፤
ተፋላሚዎቹ የሱዳን ጦር ሰራዊትና የፈጥኖ ደራሹ ሀይሎች መሪዎች የስብሰባውን ውሣኔዎች እንደሚያክበሩና ተግባራዊም እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸው ተገልጿል። ሆኖም ግን ሁለቱም ሀይሎች ከዚህ ቀደም ተስማምተው የፈረሟቸውን ስምምነቶችን በመጣስ የሚታወቁ በመሆናቸው ብዙዎች መግለጫዎቻቸውን በጥርጣሬ ነው የሚያዩት።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ