1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ መስተዳድር የለዉጥ ሒደት

ማክሰኞ፣ የካቲት 19 2011

የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶሕዴፓ) መሪዎች መካከል የተፈጠረዉን ዉዝግብ ለማስወገድ በቅርቡ አጠቃላይ ጉባኤ እንደሚደረግ የክልሉ  ባለስልጣናት አስታወቁ።ባለፈዉ ጥር ተካርሮ የነበረዉ ዉዝግብ በክልሉ የተጀመረዉን ለዉጥ ያደናቅፈዋል የሚል ሥጋት አስከትሎ ነበር።

https://p.dw.com/p/3E7Nj
Äthiopien Stadt Jijiga
ምስል DW/T. Waldyes

(Beri.DD) Somalie region reform - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ገዢ ፓርቲ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶሕዴፓ) መሪዎች መካከል የተፈጠረዉን ዉዝግብ ለማስወገድ በቅርቡ አጠቃላይ ጉባኤ እንደሚደረግ የክልሉ  ባለስልጣናት አስታወቁ።ባለፈዉ ጥር ተካርሮ የነበረዉ ዉዝግብ በክልሉ የተጀመረዉን ለዉጥ ያደናቅፈዋል የሚል ሥጋት አስከትሎ ነበር።የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር አቶ አደም ፋራሕ ግን  ዉዝግቡን «የሐሳብ ልዩነት» በማለት አሳንሰዉታል።አቶ አደም ከድሬዳዋዉ ወኪላችን መሳይ ተከሉ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ እንዳሉት አዲሱ መስተዳድራቸዉ በቀዳሚ መስተዳድር የፈረሱ የአስተዳደር መዋቅሮችንና የፀጥታ ኃይሉን ዳግም አደራጅቷል።

መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ