የሶማሌ እና የአማራ ሕዝቦች የውይይት መድረክ ተካሔደ
እሑድ፣ ሐምሌ 14 2011ማስታወቂያ
የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሐመድ ዑመር እና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው በተገኙበት በዛሬው ዕለት የሶማሌ እና የአማራ ሕዝቦች የውይይት መድረክ ተካሒዷል። ውይይቱ የተካሔደው በባሕር ዳር ከተማ ነበር። ውይይቱን የተከታተለው ዓለምነው መኮንን ተጨማሪ ዘገባ አለው።