1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ ክልል የጋራ ምክክር መድረክ ለሰላም

ዓርብ፣ መስከረም 21 2014

የሶማሌ ዑጋዞች፣ ገራዶች ወበሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ስለማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች ግጭት እና ግጭቱ ባስከተላቸው ችግሮች ላይ መክረዋል። ግጭቱ በክልሉ ምዕራብ ሲቲ ዞን በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ በርካታ ጉዳቶች አድርሷል ያለው የጋራ ምክክር መድረክ በተለለያዩ ጉዳዮች ላይ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

https://p.dw.com/p/419JA
Äthiopien | Konflikte zwischen den Regionen Afar und Somali
ምስል Mesay Tekelu/DW

ውይይቶቹ እስካሁን ተጨባጭ ውጤት አላመጡም

የሶማሌ ዑጋዞች፣ ገራዶች ወበሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች ለዓመታት ዘላቂ ዕልባት ባልተበጀለት የሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች ግጭት እና ግጭቱ ባስከተላቸው ችግሮች ላይ መክረዋል። ግጭቱ በክልሉ ምዕራብ ሲቲ ዞን በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ በርካታ ጉዳቶች አድርሷል ያለው የጋራ ምክክር መድረክ በተለለያዩ ጉዳዮች ላይ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። የሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሄን ለማምጣት በየጊዜው ውይይቶች ቢካሄዱም ተጨባጭ ውጤት ግን ያመጣ አይመስልም።

የሂሳ ዑጋዛዊ ምክር ቤት ተወካይ አቶ መሀመድ ሙሴ ጌሌ የሶማሌ ዑጋዞች፣ ገራዶች፣ ወበሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት በማካሄድ አውጥተውታል ባሉት መግለጫ ግጭቱ በተፈጠባቸው የምዕራብ ሲቲ ዞን አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ሰዎች የክልሉ ማኅበረሰብ  ድጋፍ እንዲደርግ የፌደራል መንግሥቱም መልሶ ተፋናቃዮችን እንዲያቋቁም ጠይቀዋል።

Äthiopien | Konflikte zwischen den Regionen Afar und Somali
ምስል Mesay Tekelu/DW

የውይይት መድረኩ በመግለጫው በሁለቱ ማኅበረሰብ መካከል ያለው ደም መፋሰስ እንዲቆም እና የተፈናቀሉ ወገኖች በአስቸኳይ እንዲመለሱ እና የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን ጠይቋል። በሁለቱ ማኅበረሰብ መካከል ላለው ግጭት ሕገመንግሥታዊ መፍትኄን የጠየቀው የሶማሌ ዑጋዞች፣ ገራዶች ወበሮች እና የሀገር ሽማግሌዎች የጋራ መድረክ የአፋር ክልል የጀመረውን አዲስ መንደር ግንባታ እንዲያቆም እና በኃይል ይዟቸዋል ካላቸው ቦታዎች እንዲወጡ ጠይቋል።

የፌደራል ፀጥታ አካላት በግጭቱ ለማንም እንዳይወግኑ እና ከአድሎአዊነት እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል። በተለያዩ ጊዜያት በሚቀሰቀስ ግጭት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ለሚገኘው የሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ዘላቂ መፍትሄን ለማምጣት በየጊዜው ውይይቶች ቢካሄዱም ተጨባጭ ውጤት ያመጣ አይመስልም።

መሳይ ተክሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ