1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሌ ፖለቲካ እና የተመላሾቹ ሚና

ሰኞ፣ ነሐሴ 14 2010

የቀድሞው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጀማል ዲርየ ኸሊፍ ከ11 አመታት የስደት ኑሮ በኋላ በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ። ለአጭር ጊዜም ቢሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባል የነበሩት አቶ ጀማል በሶማሌ ክልል ፖለቲካ፣ በተቋማት ግንባታ እና ሰላም ለማውረድ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመሳተፍ ዕቅድ አላቸው።

https://p.dw.com/p/33RQc
Jemal Deere Kelif
ምስል privat

Q&A Former Ethiopian PM is going home to take part in hot regional politics - MP3-Stereo

አቶ ጀማል ሐሳባቸውም ሆነ በሕግ እና በሥርዓት የሚመራ መንግሥታዊ መዋቅር የመፍጠሩ ሒደት አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ እርግጠኛ ናቸው። እንደ አቶ ጀማል ሁሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ተቃዋሚዎች፣ የሰብዓዊ መብት እና የለውጥ አቀንቃኞች ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ብሎም ወደ ጅጅጋ በመመለስ ላይ ይገኛሉ። በቅርቡ ስሙ ከሽብርተኝነት ዝርዝር የተሰረዘው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር አመራሮችም ኢትዮጵያ ገብተዋል። አቶ ጀማል እና በስደት የቆዩ ፖለቲከኞች ወደ ኢትዮጵያ ምን ይሰሩ ይሆን? አቶ ጀማል ሐሳባቸውን አጋርተውናል። 

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሀመድ