የሶማሌና የአፋር ክልል ውዝግብ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 21 2013የሶማሌ እና አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሮችን ዓመታት ለዘለቀ እሰጥ አገባ የዳረጉት አዋሳኝ ሦስት ቀበሌዎች አንዱ መሆኑ በሚነገርለት ገርበኢሴ ቀበሌ ከሦስት መቶ በላይ ንፁሐን ዜጎች ከቀናት በፊት ተገድለዋል ያለው የሶማሌ ክልል ድርጊቱን ባወጣው መግለጫ ኮንኗል፡፡ በአፋር ክልል የሚገኘው የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር በበኩሉ በሶማሌ ክልል የቀረበው መግለጫ በመረጃ የተደገፈ አይደለም ብሏል። የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሮብሌ ለDW በስልክ በሰጡት መግለጫ በአፋር ልዩ ኃይል እና በክልሉ በሚንቀሳቀሰው ኡጉጉሙ የተባለ ታጣቂ ቡድን ገርበኢሴ በተባለ ቀበሌ ፈፅሞታል ባሉት ጭፍጨፋ በርካቶች ሞተዋል፤ የተቀሩትም ከቀየው ወተዋል፡፡ ከአካባቢው ኅብረተሰብ አገኘን ባሉት መረጃ መሰረት ከሦስት መቶ እስከ አራት መቶ የሚጠጉ ንፁሐን ተገለዋል ብለዋል፡.የፌደራል ሠራዊት በአካባቢው እያለ በንፁሐን ላይ የተፈፀመው ጥቃት አግባብ አይደለም ያሉት አቶ መሀመድ በአሁን ሰዓት ክልሉ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ በመስጠት ህይወታቸው ያለፉ ዜጎችን ቀብር እያስፈፀመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ክልሉ ጥቃቱን በተመለከተ መረጃ ነበረው ያሉት አቶ መሀመድ ሀገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሌላ የኃይል እርምጃ ከመወሰድ ተቆጥበናል፤ ነገር ግን እንዲህ ያለው ሁኔታ በዚሁ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ እናስብበታለን እስካሁን እያደረግን ያለነው መከላከል ብቻ ነው ብለዋል፡፡
በአፈር ክልል በኩል በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ የክልሉ ፀጥታ ኃላፊ አቶ መሀመድ በበኩላቸው ሥራ ላይ እንደሆኑ በመግለፅ ምላሽ እነደማይሰጡ ተናግረዋል።
ይኽን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው
በአካባቢው ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ የባቡር እና የብስ ትራንስፖረት መስመሮች መዘጋታቸውን የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጠቁመዋል የአካባቢው ሰላም ወደ ቀድሞ ሁኔታው አለመመለሱን አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል፡፡
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ