የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተግዳሮት
እሑድ፣ ሰኔ 12 2014ኢትዮጵያ ውስጥ የዛሬ አራት ዓመታት ገደማ የተሻለ መረጋጋት እና ሰላማዊ ኑሮ እንደሚመጣ በማሰብ ተስፋው ለምልሞ የታየው የሀገሪቱ ሕዝብ አሁንም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሰላም እጦት ስጋት ላይ እንደሚገኝ ይሰማል። ከሀገሪቱ የሚወጡ ዜናዎችም የጦርነት ግጭት፤ የሞት እና መፈናቀል እንዲሁም እስራት እና መዋከብ ከሆኑም ሰነባብተዋል። ዘመናት ላስቆጠረውም ሆነ አሁን ላለው ግጭት ጦርነት መንስኤ ናቸው ተብሎ ለሚታሰቡ ኹነቶች መፍትሄ እንዲሆን የብሔራዊ መግባባት ጥሪ ሲቀርብ ቆይቷል። በቅርቡም የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ተቋቁሞ በምክር ቤት ጸድቆ ሥራ ጀምሯል። ሆኖም የኮሞሽኑን መመስረት የደገፉ እንዳሉ ሁሉ፤ የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተጠሪነት ገዢው ፓርቲ ለሚበዛበት ምክር ቤት መሆኑን አጽንኦት በስጠት ከአመሠራረቱ ጀምሮ ገለልተኝነቱ ላይ ጥያቄ ያነሱም ጥቂት አይደሉም ። ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ገና ወደ ዋናው ሥራው ሳይገባ የሚታየው ተቃውሞ እና ክፍፍል ተስፋ የተጣለበትን ሀገራዊ ጉዳይ ሊያሰናክለው ይችላል የሚል ስጋት አሳድሯል። ሁሉንም ወገኖች የሚያግባባ አካል እንዴት ነው ሊኖር የሚችለው? በኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን የፖለቲካ ተዋናዮች ሚናስ እስከምን ድረስ ይኾን?
ዶቼ ቬለ በጉዳዩ ላይ ሦስት እንግዶችን ጋብዞ አወያይቷል።ተወያዮች ዶክተር ዮናስ አዳዬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንገር፣ ኦፌኮ ሥራ አስፈጻሚ አባል እንዲሁም ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት የሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የእስትራቴጂ ጉዳይ ኃላፊ ናቸው። ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሸዋዬ ለገሠ