የብሔራዊ ዉይይትና የፖለቲከኞች ፍላጎት
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 15 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት «ሐገራዊ ምክክር» ያለዉን ብሔራዊ ዉይይት እንዲመራ የታሰበዉ ኮሚሽን ገለልተኝነቱ መረጋገጥ እንዳለበት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እየጠየቁ ነዉ።ይሁንና ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸዉ ፖለቲከኞች የዉይይቱን አስፈላጊነት ያምኑበታል።ነፍጥ አንግበዉ የሚዋጉ ኃይላት በዉይይቱ መካፈል አለመካፈላቸዉን ግን እያጠያየቀ ነዉ።ዉይይቱን የሚመራዉ ኮሚሽን የሚመሠረትበት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ዉይይት እየተደረገበት ነዉ።የኮሚሽኑ የስራ ዘመን ለሶስት ዓመታት ይፀናል ተብሏል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ