1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪክስ አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ውጥን፣ እድል ወይስ ፈተና?

ሰኞ፣ ጥቅምት 18 2017

አገራቱ በስብሰባቸው ትኩረት አድርገው ከመከሩባቸው በርካታ ጉዳዮች አንደኛውና በዋናነት ትኩረትን የሳበው ሃሳብ ለዓለማቀፍ ግብይት በዶላር ላይ የሚደረገውን ጥገኝነት የመቀየስ ዘዴ ለማምጣት የወጠኑት ነው፡፡ በዚህም አዲስ የብሪክስ አባል አገራት መገበያያ ገንዘብ ተሰርቶ በአገራቱ መካከል ለሚደረግ ንግድ አገልግሎት ላይ እንዲውል ነው የታሰበው፡፡

https://p.dw.com/p/4mJxA
Russland Kasan 2024 | Wladimir Putin und Cyril Ramaphosa beim BRICS-Gipfel
ምስል Iranian Presidency/ZUMA/picture alliance

የብሪክስ አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ውጥን እድል ወይስ ፈተና?

የብሪክስ አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ውጥን እድል ወይስ ፈተና?

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን አሰባስቦ የተመሰረተው BRICS የአገራት ማህበር ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ሳውዲአረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ማህበሩን ከተቀላቀሉ ወዲህ የመጀመሪያውን ጉባኤውን ባለፈው ሳምንት ውስጥ በሩሲያ ሰብሳቢነት አካህዶ ነበር፡፡ አገራቱ በስብሰባቸው ትኩረት አድርገው ከመከሩባቸው በርካታ ጉዳዮች አንደኛውና በዋናነት ትኩረትን የሳበው ሃሳብ ለዓለማቀፍ ግብይት በዶላር ላይ የሚደረገውን ጥገኝነት የመቀየስ ዘዴ ለማምጣት የወጠኑት ነው፡፡  በዚህም አዲስ የብሪክስ አባል አገራት መገበያያ ገንዘብ ተሰርቶ በአጋራቱ መካከል ለሚደረግ ንግድ አገልግሎት ላይ እንዲውል ነው የታሰበው፡፡ በርግጥ የአገራቱ ማህበር “de-dollarisation” ያሉትና ዶላር ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያመጡት አጀንዳ አገራቱ ካላቸው አቅም አንጻር ልሰራ ብችልም ለጊዜው የሚሆን ነው ወይ በሚል ጥያቄም ጥርጣሬም የሰነዘሩ በርካቶች ናቸው፡፡ የምጣኔ h,ብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው ዓለሙ በዚህ ላይ በሰጡን አስተያየት የውጥኑ መስራት አለመስራት ወይም ውጤታማነት በአባላቱ መካከል ከአገር አገር ይለያያል ነው የሚሉት፡፡

ብሪክስ ለአፍሪካዉያን የሚገባቸውን ቦታ ይሰጣቸው ይሆን?

 

 

በካዛን ሩስያ የተካሄደው የዘንድሮው የብሪክስ ጉባኤ
በካዛን ሩስያ የተካሄደው የዘንድሮው የብሪክስ ጉባኤምስል Maxim Shipenkov/AP/picture alliance


“ነገሩን ከኢትዮጵያ አኳያ ስንመለከተው እኛ በብዛት ብድር ፈላጊ ነን” የሚሉት ዶ/ር አጥላው ብድሩ በብዛት የምገኘው ከምዕራቡ ዓለም እንደመሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት ከዶላር ተጽእኖ መላቀቅ ቀላል እንደማይሆን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራ ከዶላር ተጽእኖ ለመውጣት አምርተው ወደ ውጪ ዌም ዓለም ገቢያ የሚላከውን ብርቱ አቅም የሚጠይቅ ስለመሆኑም ባለሙያው በአስተያየታቸው አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተቃራኒው “አምርተው ወደ ውጪ ገቢያ የመላክ እምቅ ላላቸው እንደ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ላሉ አገራት ግን ውጥኑ ሳይሰራ አይቀርም” ያሉን ባለሙያቀው እነሱ እርሰበርስ መነጋገድ ሚያስችላቸው አቅም ስላላቸው ምናልባት የዶላርን ተጽእኖ የመቀነሱ ሃሳብ በእነሱ ዘንድ ገቢራዊ ሊሆን እንደምችልም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በይፋ ብሪክስን ስትቀላቀል ባለሙያዎች ስለ ፋይዳው ጥርጣሬ ገብቷቸዋል
የብሪክስ አባል አገራት በተለይም በማህበሩ ውስጥ የጎላውን ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉ ቻይና እና ሩሲያ ለዓለማቀፍ ንግድ መገበያያ ይረዳል የተባለውን የብሪክስ መገበያያ ሃሳብ ለማምጣት የተገደዱበት አንዱ ምክንያት፤ አሜሪካ በሁለቱ አገራት ላይ ለከፈተችው የንግድ ጦርነት መልስ እንዲሆናቸው በማሰብም ነው በሚል ይጠቀሳል፡፡

በካዛን ሩስያ የተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ
በካዛን ሩስያ የተካሄደው የብሪክስ ጉባኤምስል Alexander Kazakov/SNA/IMAGO

የመገበያያ ገንዘቡ ውጥንና የወጪ ንግድ አቅም አስፈላጊነት

የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ እንደ አባልነቷ በዚህ በተወጠነው ሂደት ተጠቃሚ ለመሆንም ሆነ ተጽእኖውን ለመቋቋም ምርትን የማምረትና ወደ ውጪ ገቢያ የመላክ አቅሟን ማሳደግ ይጠበቅባታልም ነው ያሉት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር አጥላው፡፡ “ዲዶላራይዜሽን ለማምጣት ምርትን የማምረት አቅምህን ማሳደግ ኖርብሃል፡፡ በተለይም ከነኚህ አባል አገራ ጋር የሚያስተሳስር ገቢያ ለማግኘት የተለያዩ አማራጮችን መመልከት ይጠይቃል” ብለዋል፡፡ አክለውም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገራት ከብሪክስ አባል አገራት ብድር የሚገኙበት መንገድ ያስፈልጋልም ያሉት ባለሙያው ህን ለማድረግ ሚያስችል ሁኔታ አለ ወይ የሚለውን መየየቅ እንደሚያስፈልግም አልሸሸጉም፡፡ ከአባል አገራቱ ጋር የሚያስተሳስር የንግድ አቅም እና የአባል አገራቱ የአበዳሪነት አቅም በጥልቀት ልታይ የሚገባ ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውንም በአስቴየታቸው አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በይፋ ብሪክስን ስትቀላቀል ባለሙያዎች ስለ ፋይዳው ጥርጣሬ ገብቷቸዋል
በኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በቅርቡ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ.ኤም.ኤፍ አራት ቢሊየን ዶላር ግድም ብድር ማጽደቋ አይዘነጋም፡፡ 

ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር