የተመድ የልማት ፕሮግራም እና ጀርመን ለሰሜን ኢትዮጵያ የ10 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ አደረጉ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን ለመርዳት የተባበሩት መንግታት ድርጅት እና የጀርመን መንግስት የ 10 ሚልዮን ዮሮ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ:: በሁለቱ ወገኖች የሚቀርበው የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን ኢትዮጵ ይደረጋል የተባለውን የሰላም ስምምነት ለማፋጠን ያግዛል ተብሏል።
ዛሬ ከቀትር በሁዋላ በኢትዮጵያ የጀርመን ኢምባሲ ቅጥር ግቤ ውስጥ በኢትዮጵያ የጀርመን አባሳደር ስቲፈን አሁሩ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉት የመንግስታቱ ድርጅት የልማት ፕሮግራም UNDP ተወካይ ቱርሀን ሳላህ መካከል ነው ስምምነቱ የተፈረመው ።
አምና በዚህ ወር መገባደጃ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2015 የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ሀይሎች በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል። የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ
ዛሬ ከጀርመን መንግስት ጋር ያደረግነው ስምምነት ይህንን ሰላም እውን ለማድረግ የሚሰራውን ስራ ያፋጥነዋል ሲሉ መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉት የ UNDP ተወካይ ቱርሀን ሳላህ ተናግረዋል። አያይዘውም «ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ሰላም ከሌለ እድገት የለም እድገት ከሌለ ደግሞ ሰላም የለም ሰለዚህ ሁለቱም የማይነጣጠል ነው ሲሉ ተናግረዋል»
«በኢትዮጵያ የጀርመን አንባሳደር አንባሳደር ስቲፍን አሁር በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም እና እድገትን ለማምጣት ለሚሰራው ስራ የጀርመን መንግስት ያደረገውን የመጀመሪያው ይሆናል ብዬ ተስፋ የማደርገውን ስምምነት ለመፈራረም በመብቃቴ በጣም ደስተኛ ነኝ» ብለው አያይዘው በጦርነት ተጠያቂ የሆኑት አካላት ለፍርድ እስካልቀረቡ ድረስ ዘላቂ ሰላም ማግኘት አይቻሉም » ሲሉ ተናግረዋል ።
በሰምምነቱ ወቅት ከጀርመን መንግስት የተለገሰው ገንዘብ በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ማለትም ለአፋር ፣አማራ እና ትግራይ ክልሎች እንደሚውል ተገልጿል ። ለተጠቀሱት ክልሎች በተናጥል የተመደበው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ እና በምን ተግባር ላይ እንደሚውል ላቀረብኩት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ተቆጥበዋል ። WFP ጀርመን ለኢትዮጵያ ድንገተኛ አደጋ 8.5 ሚሊዮን ይሮ መለገስዋን አወደሰ
በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች ሁለት ዓመት ገደማ በተካሄደው ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን ማጣታቸውን እና የ29 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የኢኮኖሚ ውድመት መድረሱ ይታውሳል ።
ሃና ደምሴ
ታምራት ዲንሳ
እሸቴ በቀለ