1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰኞ ታኅሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት

ሐይማኖት ጥሩነህ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 14 2017

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ በመጨረሻም ታዋቂውን አትሌት ስለሺ ስህንን አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል። በጀርመን ማግድቡርግ መሀል ከተማ በሚገኝ የገና ገበያ ላይ የተፈጸመ ጥቃት የቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ የሀዘን ድባብ ፈጥሯል።

https://p.dw.com/p/4oVqm
Bayern München - RB Leipzig | Schweigeminute nach dem tödlichen Anschlag auf dem Weihnachtsmarkt in Magdeburg
ምስል Sven Hoppe/dpa/picture alliance

የሰኞ ታኅሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት

 

የብዙዎችን ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ በመጨረሻም ታዋቂውን አትሌት ስለሺ ስህንን አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል። ጠቅላላ ጉባኤው ታዋቂዋ አትሌት መሠረት ደፋር የተካተተችበትን አዲስ የስራ አስፈጻሚ አባላትን በመምረጥ ጭምርም ተጠናቋል። የዛሬው የስፖርት ዝግጅት በምርጫውና በአዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አመራር የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ የባለሞያ አስተያየት አካቷል።

የታኅሣሥ 7 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

በጀርመን ማግድቡርግ ከተማ መሀል በሚገኝ የገና ገበያ ላይ የተፈጸመ ጥቃት በፈጠረው የሀዘን ድባብ የተካሄደውን የቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ጨዋታም ሌላ የስፖርት ዝግጅት ትኩረት ነው። የእንግኪዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ውጤቶችም ይቀርባሉ።


ሐይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ