1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታኅሳስ 19 ቀን 2017 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 19 2017

የተመ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮን አጸደቀ። ኢትዮጵያ ከአትሚስ ወደ አዲሱ ተልዕኮ የሚደረገው ሽግግር “ስኬታማ የሚሆነው የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች ሙሉ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከተጠናከሩ ብቻ ነው” ብላለች። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኬንያ የተስፋፋውን የግለሰቦች አፈና ለማቆም ቃል ገቡ። የእስራኤል ጦር በሰሜን ጋዛ ሥራ ላይ ከነበሩ የመጨረሻዎቹ ሆስፒታሎች የአንዱን ዳይሬክተር ማሰሩን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን መከስከስ በፍጥነት እና በገለልተኝነት እንዲመረመር የአውሮፓ ኅብረት የውጪ ጉዳይ ኃላፊ ካያ ካላስ ጥሪ አቀረቡ።

https://p.dw.com/p/4oeQ5
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።