የትግራይና የአማራ መሪዎች መግለጫ
ረቡዕ፣ ጥር 8 2011ማስታወቂያ
የአማራና የትግራይ መስተዳድሮች መሪዎች ትናንት በጋራ የሰጡት መግለጫ በሁለቱ መስተዳድሮች መካከል እየተካረረ የመጣዉን አለመግባባት ለማርገብ ይረዳል የሚል አስተያየት እየተሰነዘረ ነዉ።የሁለቱ መስተዳድሮች ፖለቲከኞች የገጠሙት እሰጥ አገባ ሁለቱን ተጎራባች ሕዝብ ከግጭት ይዶለዋል የሚል ሥጋት አሳድሯል።የአማራ ርዕሠ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸዉና የትግራይ ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ትናንት የሐይማኖት አባቶችና የሐገር ሽማግሌዎች በተገኙበት በሰጡት መግለጫ ግን ለጠብ የሚጋብዝ ልዩነት እንደሌላቸዉ አስታዉቀዋል።የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት መግለጫዉ ከልብ ከሆነ ሥጋቱ ይወገዳል።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋለም አልደየስ