የአሜሪካ ገንዘብ ዕቀባና የአምባሳደር ሺን ተቃውሞ
ዓርብ፣ ነሐሴ 29 2012ማስታወቂያ
የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይ በያዘችው አቋም ምክንያት ለመስጠት ካቀደው የገንዘብ ድጋፍ 130 ሚልዮን ዶላር በድንገት መቀነሱ፤ የአሜሪካ ወዳጅ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ የተፈፀመ እጅግ አሳዛኝ እና ታላቅ ስህተት መሆኑን አንድ ከፍተኛ የቀድሞ የአሜሪካ ዲፕሎማት ገለፁ። በኢትዮጵያ የዩናይትድስቴትስ የቀድሞ አምባሳደር ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን በተለይ ለዶይቼ ቨለ "DW" እንደገለፁት ፤ የህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያ በአንድነት ያስተሳሰረ በመሆኑ የድጋፍ ዕቀባው ፈፅሞ የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም። ውሳኔው በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ነዋሪ የሆነው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊው ማኅበረሰብ ፀረ-ትራምፕ የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንዲጀምር የሚያነሳሳውና ፤ በመጪው ኅዳር ወር በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫም ድምፁን በመንፈግ በውጤቱ ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ዝርዝሩን የፍራንክፈርቱ ዘጋቢያችን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ