1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

አሜሪካ ፕሬዝደንታዊ የምርጫ ውጤት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2017

የዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ የሀገሪቱን 47ኛ ፕሬዝደንት ወሳኝ በሆነው ድምፁ መርጧል። እንደ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ የፍጻሜ ፉክክር የብዙዎችን ቀልብ በሳበው የአሜሪካ ምርጫ ከዚህ ቀደም ዋይትሀውስን ለአራት ዓመታት የሚያውቁት ቱጃሩ ዶናልድ ትራምፕ ለቀጣይ አራት ዓመታት ሊኖሩበት ከደጃፉ ቆመዋል።

https://p.dw.com/p/4miGA
US-Wahl 2024 | Florida | Republikanische Partei | Donald Trump in West Palm Beach
ምስል Brendan McDermid/REUTERS

አሜሪካ ፕሬዝደንታዊ የምርጫ ውጤት

 ዶናልድ ትራምፕ በርካታ ከባድ ክሶች ቀርበውባቸው፤ በ34 ክሶች ጥፋተኛ በመባላቸው የምርጫ ድላቸውን ታሪካዊ አድርጎታል። በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል ክሶች ጥፋተኛ የተባለ ፕሬዝደንት ሆኖ በዓለም ወሳኝ የሆነውን ሥልጣን ሲይዝ የመጀመሪያው ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። አነጋጋሪ የውጪ ፖሊሲያቸውን ጨምሮ በሀገር ውስጥም እንዲሁ ወግ አጥባቂ አቋማቸው ተፎካካሪያቸውን በከፍተኛ የድምፅ ልዩነት ለማሸነፍ ያስችላቸዋል ብሎ የገመተ ብዙ አልነበረም። በዚህ ምርጫ ትራምፕ በሀገሪቱ 50 ግዛቶች ከ270 በላይ ድምፅ በማግኘት ተፎካካሪያቸውን አሸንፈዋል። ተቀናቃኛቸው ዴሞክራቷ  ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስ 219 ድምፅ ላይ መቆማቸው አሜሪካ ዛሬም ለሴት ፕሬዝደንት ዝግጁ እንዳልሆነች ያመላከተ መስሏል። በነገራችን የዛሬ ስምንት ዓመትም ትራምፕ ሴት እጩ ተፎካካሪያቸውን ሂላሪ ክሊንተንን አሸንፈው ነበር ወደ ዋይትሃውስ የገቡት። የምርጫ ውጤቱ በአሜሪካው ዘንድ እንዴት እየታየ ነው ?  ከዋሽንግተን ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ በቀጥታው ስርጭት መስመር ላይ አነጋግረናል።  ቃለመጠይቁን ከድምጽ ማዕቀፉ ያድምጡ።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ