1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቃል

ረቡዕ፣ ግንቦት 22 2010

«መታሠሬ በሕይወቴ ልጽፈው የማልችለውን መጽሐፍ እንድጽፍ ረድቶኛል። የሕዝቡ መልካም እና ደማቅ አቀባበልም አኩርቶኛል።» ሲሉ ትናንት ከእስር ቤት የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ገለጹ።

https://p.dw.com/p/2ye06
Äthiopien Oppositioneller Andargachew Tsige  begnadigt
ምስል DW/Yohannes Gebreegziabher

«የጻፍኩት መጽሐፍ ኮፒ ከተሰጠኝ ለሕዝብ ይጠቅማል»

በእስር ቆይታቸው በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የጻፉት መጽሐፍ መኖሩን በማመልከትም ኮፒው የሚሰጣቸው ከሆነ ሕዝብ ቢያነብበው እንደሚጠቅምም ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው ዛሬ በተለይ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሕዝቡ ላደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል። ያነጋገራቸው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ