የአወዛጋቢው ዳኛ ሹመት በአሜሪካ
ሰኞ፣ መስከረም 28 2011ማስታወቂያ
ሀገሪቱን የሚያስተዳድሩት የሪፐብሊካን እና ዴሞክራት የሕዝብ እንደራሴዎች ክፉኛ የተከፋፈሉባቸው ብሬት ካቫኖ ከትናንት በስተያ ከተሾሙበት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኝነታቸው አረፍተ ዘመን ካልገታቸው በቀር ለቀጣይ 3 አስርት ዓመታት ሊከርሙበት እንደሚችሉ ነው የተነገረው። በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቋሚነት የመጡት እና የሪፐብሊካኖች ሙሉ ድጋፍ ያላቸው ዳኛ ሲመት ገለልተኛ ለሚባለው ለሀገሪቱ የፍትህ ሥርዓት ምን ማለት ይሆን? ከዋሽንግተን የመገናኝ ብዙሃንን አስተያየት የቃኘው መክብብ ሸዋን ባጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ