የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእስልምና በዓላት አከባበር ላይ ጥናት አካሄደ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2016
በዚህ ዓመት ራስ-ገዝ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ የመውሊድ በዓል የአከባበር ስርዓትና ባህላዊ ገፅታን ለመሰነድ የሚያስችል ጥናት ማስጀመሪያ ውይይት አካሂደ ።የዕምነቱ ተከታዮች፣ ምሁራን እና ሌሎች አካላት በተገኙበት የተካሄደው የጥናት ማስጀመሪያ መድረክ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመውሊድን በዓል ሲያከብሩ በበዓሉ ቀንና ከበዓሉ በኋላ የሚተገብሯቸው ስርዓቶችን ከባህል ጥናት አንጻር ምን እንደሚመስሉ ብሎም ይህንን ልዪ የማህበረስባዊ ክንውን በአለም በማይዳሰሱ ሀብቶች እንዲመዘገብ ለማድረግ የሚያስችል ሂደት ማስጀመሪያ ይሆናል ተብሎዋል።
የመውሊድ በአል አከባበር በኢትዮጵያ ከ ዋዜማው እስከ ማግስቱ ያለው ስርአት ልዪ ነው ይላሉ ጥናት አቅራቤዎች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመውሊድ በዐልን ሲያከብሩ አማኙንም ከምነቱ ውጭ ያሉትም የሚጋብዝ ማህበራዊ በአል ነው።በአሉ በተቁዋም ፣በማህበር ፣በመስኪድ እና በግለስብ ደረጃ ሊከበር ይችላል፣ በዚህ ልዪ ማህበራዊ መስተጋብር ሂደት አንድ ሰው ቂም በሆዱ ይዞ አብሮ አይቀመጥም፣ ቂሙን ሽሮ እንጂ ሲሉ የመውሊድ በአልን የተለየ አከባበር ፣የእርቅ ሄደቱን እና የቡና ስር አቱን፣ በአማረኛ እና በአረበኛ የሚዘየሩ መንዙማዎችን ያነሱት ዶ/ር መሀመድ አሊ የመውሊድን ጥበባዊ መገላጫዎች አስረድተዋል።
በአዲስ አበባ ባህል ፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቤሮ ምክትል ሀላፊ የሆኑት አቶ ሰርፅ ፍሪ ስብሀት በኢትዮፕያ በመውሊድ ግዜ የሚዘየሩት መንዙማዎች እስካሁን ያልተበርዙ እና ያልተከለሱ ፍፅም ኢትዮጵያዊ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል አያይዘውም በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተደመጡ ያሉ መንዙማዎች ላይ የሚታየውን የይዘት ለውጥ ወጥነቱን ሊያጠፋው ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ የማህበራዊ እና ባህል ተመራማሪ ዶ/ ር ሳሙኤል ጥበበ ለ DW እንደተናገሩት ውይይቱ ጥናቱን ማስጀመርያ እና ይህን ባህላዊ ክንውን በዪኔስኮ ለማስመዝገብ መደላድል ነው ብለዋል አክለውም በኢትዮጵያ አቃፊ ያልሆነ ባህል የለም ሲሉ አብራርተዋል ።የሸዋል ኢድ በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡ ሀረሪዎችን አስደስቷል
መስቀል፣ ፊቼ ጨንበላላ፣ የገዳ ስርዐት፣ ጥምቀት ፣በተጨማሪ በቅርቡ የተመዘገበውን ሽዋሊድ ጨምሮ የኢትዮጵያ የማይዳሰሱ ሀብቶች ቁጥር 5 ደርሰዋል።
ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ሃና ደምሴ
ፀሐይ ጫኔ
ሂሩት መለሠ