1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፋርና የሶማሌ ክልል ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 20 2013

የአፋርና የሶማሌ ክልሎች ባለስልጣናት ሰሞኑን በተለያየ ሥፍራ «ተፈፀመ» ላሉት ጥቃት እንዱ የሌላዉን ወገን እየወቀሰ ነዉ......የሁለቱም ክልሎች ባለስልጣናት ጂጂጋና ሠመራ ሆነዉ ያሉትን ከማለት ዉጪ ደረሰ ስላሉት ጉዳት መጠን፣ ስለተጎዳዉ ሰዉ ብዛትም ያሉት ነገር የለም

https://p.dw.com/p/3nKtL
Karte Äthiopien Ethnien EN

የአፋርና የሶማሌ ክልሎች ባለስልጣናት ሰሞኑን በተለያየ ሥፍራ «ተፈፀመ» ላሉት ጥቃት እንዱ የሌላዉን ወገን እየወቀሰ ነዉ።የሶማሌ ክልል ባለስልጣናት የአፋር ታጣቂዎች በተለይም አፍደም ወረዳ ዉስጥ ሰርገዉ ገብተዉ ሠላማዊ ሰዎችን ገድለዋል፣ አቁስለዋልም ይላሉ።የአፋር ክልል ባለልጣናት ባንፃሩ ጥቃቱ የደረሰዉ በአፋር ክልል ገዋኒ ወረዳ፣ አጥቂዎቹም የሶማሌ ክልል ታጣቂዎች ናቸዉ ባዮች ናቸዉ።የሁለቱም ክልሎች ባለስልጣናት ጂጂጋና ሠመራ ሆነዉ ያሉትን ከማለት ዉጪ ደረሰ ስላሉት ጉዳት መጠን፣ ስለተጎዳዉ ሰዉ ብዛትም ያሉት ነገር የለም።ሁለቱ ተጎራባች ክልልሎች ተመሳሳይ ባሕልና ዕምነት የሚከተል፣ ተቀራራቢ የምጣኔ ሐብት ደረጃ ላይ የሚገኝ ሕዝብ የሚኖርባቸዉ፣ በአንድ ፓርቲ፣ በብልፅግና ሹማምንታት የሚተዳደሩ ናቸዉ።

 መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ