የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ
ቅዳሜ፣ ጥር 26 2004ማስታወቂያ
18ኛዉን የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ካስተናገደችዉ ከመዲና አዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ የለቱ ትኩረት በአፍሪቃ ርዕስ ነዉ። በሁለት መቶ ይሮ ወጭ ታንጾ ከቻይና መንግስት ለህብረቱ የተበረከተዉ ግዙፍ ህንጻ ዉስጥ ለመጀመርያ ግዜ የተሰበሰቡት የአፍሪቃ ህብረት መሪዎች፣ በሁለቱ ቀናት ጉባኤያቸዉ ምንን ተወያዩ የሚለዉ ይሆናል፣ ይልቱ ርዕስ። ህብረቱ የቤኒኑን ፕሪዝደንት ቶማስ ቦኒ ያዪን አዲሱ የህብረቱ ሊቀመንበር ሲሉ መሾማቸዉ ይሚታወቅ ሲሆን፣ ለህብረቱ ኮሚሽን አዲስ ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ሳይቻል ቀርቶ ፣ ከረጅም ክርክር በኻላ ፣ ዣንግ ፒንግና ሥልጣናቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ተወስኗል። በሌላ በኩል በያዝነዉአመት ህብረቱ ይተመሰረተበትን ሃምሳኛ አመት ያከብራል።
ታደሰ እንግዳዉ
አዜብ ታደሰ