የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ
ሰኞ፣ ጥር 20 2005ማስታወቂያ
የተመድ ዋና ፀሐፊ ፓን ኪ ሙንም ጭምር የተሳተፉበት ጉባዔው በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ፡ በማሊ፡ በጊኒ ቢሳው፡ በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ፡ በሶማልያ ፡ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል ስለቀጠሉት ውዝግቦች በሰፊው መክሮዋል። የአፍሪቃ ለውጥ እና ህዳሴ የሚል ርዕስ በያዘው በዚሁ ጉባዔ ንግግር ያሰሙት የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ንካኦሳዛና ድላሚኒ ዙማ አህጉሩን ቀስ በቀስ ወደ ውህደት ለማድረስ ለሚቻልበት አሰራር ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተለያዩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ተሰጥተዋል። በአህጉሩ ግጭት እየተካሄደባቸው የሚገኙ ማሊንና ዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ የመሳሰሉት ሀገራት ጉዳይ መግጫዎቹ ያተኮሩ ናቸው። በመግለጫዎቹ የተነሱትን ሀሳቦች ባጭሩ እንዲያብራራልን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት ጠይቄው ነበር።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ