የኢትዮ፣ ኤርትራ አሜሪካዉያን ድምፅ
ዓርብ፣ ጥቅምት 26 2014ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ለቨርጂኒያ ግዛት አገረገዢነት ባለፈዉ ማክሰኞ በተደረገዉ ምርጫ የወግ አጥባቂዉ የሪፐብሊካን ዕጩ ግሌን ዮንኪን አሸንፈዋል። ለበርካታ ዓመታት የዴሞክራቲክ ፓርቲ ፖለቲከኞች ሲፈራረቁበት የነበረዉን ሥልጣን አሁን የሪፐብሊካኑ ዕጩ ለመያዝ የበቁት ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያንና ሌሎች አፍሪቃ አሜሪካዉያንን አስተባብረዉ ድምፅቸዉን ለሪፐብሊካኖቹ በመስጠታቸዉ ነዉ ተብላሏል። የኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ማሕበረሰብ አባላት እንዳሉት መራጮቹ ለሪፐብሊካኑ ድምፅ የሰጡት ወይም ዴሞክራቶቹን ድጋፍ የነፈጉት የፕሬዝደንት ጆ ባይደን መስተዳድር በኢትዮጵያ ላይ ያሳደረዉን ጫና ለመቃወም ነዉ።
ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ