1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ትኩረት ምን ሊሆን ይገባል?

ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2014

ውይይት ከሁለት ወር በፊት ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በኅብረተሰቡ መካከል መተማመንን ለማጎልበትና ምቹ የውይይቱ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሊያተኩርባቸው የሚገቡ መሰረታዊ መርሆችን የተመለከተ ነበር።ስር የሰደዱ የማኅበረሰብና የፖለቲካ ልዩነቶችን በመፍታት ረገድ የክልላዊና አካባቢያዊ ተዋናዮች ሚናና ሃላፊነትም በውይይቱ ተነስቷል።

https://p.dw.com/p/4BCK7
Äthiopien Parlament Addis Abeba
ምስል Solomon Muche/DW

የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ትኩረት ምን ሊሆን ይገባል?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ውይይት እንዲሳካ ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ትናንት ለንደን ውስጥ ውይይት ተካሄደ ።መቀመጫውን ለንድን ብሪታንያ ያደረገው ቻተተምሀውስ ሮያል ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የሚባለው ተቋም ያዘጋጀው ይኽው ውይይት ከሁለት ወር በፊት ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን  በኅብረተሰቡ መካከል መተማመንን ለማጎልበትና ምቹ የውይይቱ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሊያተኩርባቸው የሚገቡ መሰረታዊ መርሆችን የተመለከተ ነበር።በውይይቱ ፣ስር የሰደዱ የማኅበረሰብና የፖለቲካ ልዩነቶችን በመፍታት ረገድ የክልላዊና አካባቢያዊ ተዋናዮች ሚናና ሃላፊነትም መነሳቱን የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ዘግቧል።  
ድልነa ጉታነህ 
ኂሩት መለሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ