የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ
ሰኞ፣ ነሐሴ 6 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ የሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ከዓመት አመት በከፍተኛ መጠን እየቀነሰ መምጣቱን የማእድን ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመሥሪያ ቤቱ የሥራ ሃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሃገሪቱ የገጠማት የፖለቲካ ቀውስ፣ ከፍተኛ የኮንትራባንድ ንግድ እና የቀልጣፋ መስተንግዶ አለመዳበር የችግሩ ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ተናግረዋል።ባለፈው አመት በሶማሌ ክልል ተገኘ የተባለው ነዳጅ በቀላሉ የሚነድ የነዳጅ አይነት መጠኑን ለመለየት ጥናት እየተደረገ እንደሆነና የምርት ሙከራ ሥራ እየተሰራ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።በሃገሪቱ ሁለት የወርቅ አምራች ኩባንያዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ሜድሮክ የተባለው ድርጅት ስራ በማቆሙ እና ኢዛና የተባለውም በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለኬሚካል እጥረት ተዳርጎ ለማምረት መቸገሩን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ