1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንግልት የሚሰንደው አዲስ ድረ-ገጽ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 2016

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበራዊ መገናኛ አውታር ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጫና እና እንግልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ። ከእስር እና ከስደት ባሻገር ጋዜጠኞች ንብረቶቻቸው በጠራራ ፀሐይ በተቀናጀ መልኩ ይመዘበራል፤ መሥሪያ ቤታቸው ቁልፍ ተሰብሮ ይበረበራል ። ተደጋጋሚ እንግልት እና በደል እንደሚፈጸምባቸውም በተደጋጋሚ ይነገራል።

https://p.dw.com/p/4duNe
Symbolbild Mikrophon auf der Bühne
ምስል picture-alliance/Bildagentur-online/Tetra

የጋዜጠኞች እስርና እንግልትን የሚሰንድ ድረገጽ ተዘጋጅቷል

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበራዊ መገናኛ አውታር ጋዜጠኞች  ላይ የሚደርሰው ጫና እና እንግልት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ።  ከእስር እና ከስደት ባሻገር ጋዜጠኞች ንብረቶቻቸው በጠራራ ጸሐይ በተቀናጀ መልኩ ይመዘበራል፤ መሥሪያ ቤታቸው ቁልፍ ተሰብሮ ይበረበራል ። ተደጋጋሚ እንግልት እና በደል እንደሚፈጸምባቸውም በተደጋጋሚ ይነገራል ።  ይህን መሰል መረጃ ግን በስርዓቱ መመዝገብ እና መሰነድ  የሚያስችል አሠራር ባለመኖሩ በተቀናጀ መልኩ ክትትል ለማድረግ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር (ኢ.አ.ማ) በመባል የሚጠራው የኤዲተሮች ማኅበር አዲስ የባለሞያዎች ጥቃት መመዝገቢያ ድረ ገፅ ወይም (portal)  አዘጋጅቶ ሥራ ላይ አውሏል ። ድረገፁ ሥራ በጀመረ በ3 ቀናት ውስጥ ብቻ ከ 13 በላይ ጥቆማዎች እንደደረሱት ዐሳውቋል ። 

ይህ ድረ-ገፅ ወይም ፖርታል በእንግሊዝኛ sojethiopia.org ይባላል በኢትዮጵያ በመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ላይ የሚደርስባቸውን ማነኛውም አይነት ጥቃት መመዝገብ የሚያስችል ነው።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO) ድጋፍ የተደረገለት እና ስራ ላይ የዋለው ይህ ፖርታል ሰዎች ከየትኛውም የሀገሪቱ ከፍል ጥቆማቸውን በአራት ቋንቋዎች መስጠት የሚያስችል ነው ። ድረገፁ ሥራ በጀመረ በ3 ቀናት ውስጥ ብቻ ከ 13 በላይ ጥቆማዎች ደርሰውናል ሲሉ  የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር ዳይሬክተር ደረሰ ንጋቱ ለ DW ታናግረዋል ።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO)
ድረገጹ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO) ድጋፍ እንደተደረገለት ተገልጧልምስል Christoph Hardt/Panama Pictures/picture alliance

በኢትዮጵያ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃንና የማኃበራዊ ሚዲያ ጋዜጠኞች ከሥራቸው ጋር  ተያይዞ  በሚደርስባቸው ጫና እስር እና እንግልት ሳብያ ብዙዎቹ  ሥራውን እየተው ፣የተቀሩት እየተሰደዱ ፣ ገሚሱ ሲታሰሩ ማየት እና መስማት እንግዳ አይደለም ። ጥቆማውን ከሰበሰብን በኋላ ቀጣዩ ሥራ ከአጋር ማኅበራት ጋር በመሆን እንሠራለን ብለዋል ዳይሬክተሩ ።

ባሳለፍነው ሳምንት የተሰደደው ኢትዮ ኒውስ የተሰኘ ድረ-ገፅ ጋዜጠኛ በለጠ ካሳ በኢትዮጵያ ያለውን ሀሳብን በነጻነት የመግለፅ ነፃነት ጀንበር ጠልቋል ሲል ለ DW ተናግሯል ።

የመጀመሪያ የሆነው sojethiopia.org የተሰኘ ድረ-ገፅ ወይም ፖርታል  በመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ሥራቸውን በሚሠሩበት ወቅት የሚደርስባቸውን ማዋከብ እንግልት ፤ እስካሁን እብዛም ትኩረት ያላገኛውን  ሴት ጋዜጠኞች በሥራ ቦታቸውም እና በሥራ  ጉዞ ላይ የሚደርስባቸውን  ፆታዊ ጥቃት ጭምር የሚመዘግብ  ማዕቀፍ ነው ።

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ታምራት ዲንሳ