1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ አፋሮች ስሞታ

ሐሙስ፣ ግንቦት 3 2009

የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኢብራሒም ሐሩን እንደሚሉት የአረብ ኤሚሬቶች የጦር አዉሮፕላኖች እስካሁን ድረስ ሃያ ሰዎችን ገድለዋል ወይም አቁስሏል

https://p.dw.com/p/2comp
Äthiopien Addis Abeba Ato Ebrahim Haron
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

(Beri.AA) Red see Afar-UAE - MP3-Stereo

 

አሰብ-ኤርትራ የሰፈረዉ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አየር ኃይል በአካባቢዉ በሚኖሩ የአፋር ተወላጆች ላይ በሚያደርሰዉ የአዉሮፕላን ድብደባ ብዙ ሰዉ መግደልና ማቁሰሉን የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አስታወቀ። የኤርትራ መንግሥትን የሚቃወመዉ የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኢብራሒም ሐሩን እንደሚሉት የአረብ ኤሚሬቶች የጦር አዉሮፕላኖች እስካሁን ድረስ ሃያ ሰዎችን ገድለዋል ወይም አቁስሏል። ሊቀመበር ኢብራሒም በአፋር ሕዝብ ላይ ይደርሳል ያሉትን በደል ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያስቆም ተማፅነዋልም። የኤርትራ አፋር ሕዝብ ከነባር ይዞታዉ እየተፈናቀለ፤ በድርቅና ረሐብ እየተሰቃየ መሆኑን ሊቀመንበሩ አስታዉቀዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ