የኤርትራ አፋሮች ጥሪና የፖለቲካ ጥያቄ
ቅዳሜ፣ ሰኔ 24 2015ኤርትራ ዉስጥ ሁሉም የሐገሪቱ ዜጎች እኩል የሚሳተፉበትና የሚጠቀሙበት ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚመሰረትበትና ፍትሐዊ ሕገ መንግስት በሚረቀቅበት ስልት ላይ የሚነጋገር ጉባኤ ነገ ሐሪስበርግ- ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ይደረጋል። የኤርትራ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የኤርትራዉያን ወዳጆች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና ምሁራን የሚሳተፉበት ጉባኤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሚመሩት ሥርዓት በኋላ ሐገሪቱ በምትመራበት ፖለቲካዊ ስርዓት እንዴትነት ላይ ይመክራል። ጉባኤዉ ጥናታዊ ፅሑፎች፣ መረጃዎችና ምክር ሐሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏልም።ጉባኤዉን ያዘጋጀዉ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) እንደሚለዉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኤርትራ መንግስት በሐገሪቱ ሕዝብ ባጠቃላይ በተለይም በኤርትራ አፋሮች ላይ የሚያደርሰዉ ግፍና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነዉ። የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ፤ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ እንዳስታወቁት በደንከሊያ (አፋር) ሕዝብ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና በደል በመሸሸሽ የሚፈናቀለዉና የሚሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን ተናግረዋል። ከ200 ሺሕ የሚበልጥ የኤርትራ አፋር ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ፣ጀቡቲና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰድዷል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ኤርትራዉያንን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ በግድ አግዟል የሚል ስለሚባለዉ ዜናን ሰምተዋል።
የኤርትራን ጉዳይ በተለይም የኤርትራ አፋሮችን አኗኗር የሚያጠኑት ካናዳዊዉ የሕግ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ኤሊዮት ማግንት በበኩላቸዉ የኤርትራ መንግስት በኤርትራ አፋሮች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ማድረሱን ጉዳዩን በተለያየ ጊዜ ያጠኑ «የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል» ይላሉ። ማግነት አክለዉ እንዳሉት የኤርትራ መንግስት የፀጥታ ኃይላት የአፋር ተወላጆችን በጅምላና በተናጥል ይገድላሉ፣ደብዛቸዉን ያጠፋሉ፣ሴቶቹን ይደፍራሉ።የኤርትራ መንግስት ሕዝቡን ከነባር ቀየዉ እየነቀለ አካባቢዉን እየተቆጣጠረ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አስታዉቀዋል።
አቶ አህመድ የሱፍ በመቀጠል ዛሬ የሚካሄደዉ ጉባኤ ፤ የኤርትራ መንግስት ያደርሰዋል የሚባለዉን የሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና በዝርዝር ተነጋግሮ ለወደፊቱ ሁሉንም የሚያሳትፍ፣ ሁሉንም በሚያግባባ ሕገ-መንግስት የሚመራ ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት የሚቻልበትን ስልት ይተልማል ተብሎ ይጠበቃል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ