1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራዉያን የነጻነት ቀን አከባበር በአትላንታ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 22 2015

በዩናይትድስቴትስ አሜሪካ፣አትላንታና አካባቢው የሚኖሩ ኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን፣የሃገሪቱን 32ኛ ዓመት የነጻነት ቀን በድምቀት ከአክብረዋል። ኤርትራና ኢትዮጵያ ለሰላም እና ዕድገት በጋራ መስራታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/4RydK
Eritrean 32 independence day celebration Atlanta
ምስል Tariku Hailu/DW

የኤርትራዉያን የነጻነት ቀን አከባበር በአትላንታ

በዩናይትድስቴትስ አሜሪካ፣አትላንታና አካባቢው የሚኖሩ ኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን፣ የሀገሪቱን 32ኛ ዓመት የነጻነት ቀን በድምቀት ከአክብረዋል። ኤርትራና ኢትዮጵያ ለሰላም እና ዕድገት በጋራ መስራታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ተገልጿል።

ኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን 32 ኛ ዓመት የነጻነት በዓላቸውን በሃገር ቤትና በባህር ማዶ እያከበሩ ይገኛሉ። እዚህ በዩናይትድስቴትስ አሜሪካ አትላንታና አካባቢው የሚኖሩ ኤርትራውያንና ትውልደ ኤርትራውያን ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ የታየበትና ደማቅ ክብረ በዓል አካሄደዋል። በዚሁ በዓል ላይ፣ንግግር ያደረጉት አቶ ተክሌ በየነ ከዶይቸ ቨለ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የአከካባቢው ሕዝቦች ተባብረው  መስራት እንዳለባቸው ሰላማቸውን ማስከበር እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

Eritrean 32 independence day celebration Atlanta
የኤርትራዉያን የነጻነት ቀን አከባበር በአትላንታምስል Tariku Hailu/DW

«ተክሌ በየነ እባላለሁ፤የአትላንታና አካባቢው የባህል ኮሚቴ ሊቀመንበር ነኝ፣የብሔራዊ ኮንግረስ የአትላንታ ቅርንጫፍ ሊቀመንበር ነኝ። በጣም ዘመኑ ስለተቀየረ ሁኔታውና ፖለቲካሊ የአፍሪቃና የእኛና የኢትዮጵያ ግንኙነት ያ ሁኔታ ቀይሮታል። ሕዝቡም እየተረዳው ነው። ሕዝቡም የኤርትራ ችግር ምን እንደነበር ምን ችግር እንደገጠማት ሁሉ ሕዝቡ ተረድቶታል።  አትላንታ ውስጥ ያለነው የኢትዮጵያና ኤርትራ ኮሚቴ አለን አብረን የምንሰራበት አለ። ከ2018 ጀምረን አብረን እየሰራን ነው።»

በኤርትራና ኢትዮጵያ መኻከል የተፈጠረው ሰላም በከባድ መስዕዋትነት የተገኘ ነው ያሉት አቶ ተክሌ፣ሰላምና መረጋጋቱ ለጋራ ዕድገታቸው ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። «ኤርትራና ኢትዮጵያ ለ80 ዓመት እያጣሉንና እያባሉን ሰላም እንዳናገኝ ያደረጉን ምዕራባውያን ናቸው። አብረን ከሰራን እናድጋለን። ሰላም የሚመስለው ነገር የለም ያለ ሰላም ደግሞ ዕድገት የሚባል የለም።»

የቀጣናው ሕዝቦች ተባብረው እስከሰሩ ድረስ፣የአፍሪቃ ቀንድ ትልቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስበት የሚሆንበት ጊዜ እየደረሰ ነው የሚሉት ደግሞ በበዓሉ ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው፣ዶክተር አሮን ከፈላ ናቸው።

Eritrean 32 independence day celebration Atlanta
የኤርትራዉያን የነጻነት ቀን አከባበር በአትላንታምስል Tariku Hailu/DW

«ከአሁን በኃላ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ውህደት ሆኖ በአንድ የምናድግበት ጊዜ እየደረሰ ይመስለኛል።እሱ ነው ትኩረት የሚሰጠው።ያው ከምዕራብ የሚመጣው ቻሌንጅ ሊቆም አይችልም።ምክንያቱም እነሱ የሚፈልጉትና የእነረሱ ፍላጎት ሁልጊዜ ለማስጠበቅ የሚሄዱበት ርቀት አለ።እኛ ግን የራሳችን ጥቅም እስካለ ድረስ ተባብረን አንድ ሕዝብ ሆነን የምንሰራው ስራ አለ። እና በተላላኪነት የሚሰራው ስራ እስኪቆም ግን ያው የራሳችንን ጥቅም ማስጠበቅ የማንችልበት ሁኔታ የለም።መአት ሪሶርስ አለ።ጠንካራ ሕዝብ አለ፣ብዙ የሚሰራ ሥራ አለ ግን እስካሁን ያ ሁሉ ርቀት ኤርትራ ብቻዋን ነው የተጓዘችው፤እና ሌሎች ሃገሮች በአጋርነት ከቆሙ ይሄን ነገር የራሳችንን ጥቅም አስጠብቀን የአፍሪቃ ቀንድ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስበት የሚሆንበት ጊዜ እየደረሰ ነው የሚል ግምት አለ በእኔ በኩል።»

ታሪኩ ኃይሉ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ