1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤች አይ ቪ ኤድስ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2012

በሀገሪቱ ከሶማሌ ፣ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች የቫይረሱ ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዳንኤል በትረ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ሴተኛ አዳሪዎችን ጨምሮ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እና መለዮ ለባሾች በከፍተኛ ደረጃ ለቫይረሱ  ተጋላጮች መሆናቸው መለየቱንም አቶ ዳንኤል ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3U9ex
Italien Welt AIDS Tag
ምስል picture-alliance/AP Photo/A. Carconi

በኢትዮጵያ ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ

በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ይሰጡት የነበረው ድጋፍ መቀነሱ ስርጭቱን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ። በሀገሪቱ ከሶማሌ ፣ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች የቫይረሱ ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በጽ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ሴተኛ አዳሪዎችን ጨምሮ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እና መለዮ ለባሾች በከፍተኛ ደረጃ ለቫይረሱ ተጋላጮች መሆናቸው መለየቱንም አቶ ዳንኤል ገልጸዋል። የዓለም የጸረ ኤድስ ቀን እሁድ ህዳር 21 ቀን 2012 ዓም በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሮ ውሏል። በኢትዮጵያ ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ታምራት ዲንሳ ከአቶ ዳንኤል በትረ ጋር ያካሄደው ቃለ ምልልስ በዛሬው ጤና እና አካባቢ ዝግጅታችን ከታች ከድምጽ ማእቀፉ በድምጽ ሙሉውን ማድመጥ ይቻላል።
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ