1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በግጭት ከ500 በላይ አባወራዎች ተፈናቅለዋል»ነዋሪዎችና የጭንሃክሰን ወረዳ ባለሥልጣናት

ሰኞ፣ ሰኔ 7 2013

ነዋሪዎች፣ በኦሮሞ ጃርሶ ጎሳ እና በሶማሊ ጊሪ ጎሳ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲሉ ተናግረዋል። የጭናክሰን ባለሥልጣናትም ባለፈው ሳምንት በተቀሰቀሰው የሁለቱ ጎሳዎች ግጭት ከ580 በላይ አባወራዎች መፈናቀላቸውን፣ የሰው ህይወት ማለፉ እና እንስሳት መዘረፋቸውን አረጋግጠዋል።

https://p.dw.com/p/3utyJ
Karte Äthiopien englisch

የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጭናክሰን ወረዳ በተለይም በዳሪሙ ቀበሌ ነዋሪዎች ከሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢ ይሰነዘርብናል ባሉት ጥቃት መፈናቀላቸውን አስታወቁ። አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት ነዋሪዎች፣ በኦሮሞ ጃርሶ ጎሳ እና በሶማሊ ጊሪ ጎሳ መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፣ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ሲሉ ተናግረዋል። የጭናክሰን ባለሥልጣናትም ባለፈው ሳምንት በተቀሰቀሰው የሁለቱ ጎሳዎች ግጭት ከ580 በላይ አባወራዎች መፈናቀላቸውን፣ የሰው ህይወት ማለፉ እና እንስሳት መዘረፋቸውን አረጋግጠዋል። ነዋሪዎች ስላቀረቡት ቅሬታ መልስ እንዲሰጡ ዶቼቬለ ለሶማሌ ክልል የቱሉ ጉለድ ወረዳ አስተዳዳሪ፤ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እና የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በመደወል ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ጥንቅር ልኮልናል።


ስዩም ጌቱ


ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ